የሰላም ስምምነቱ ፍልስጤምን ሊያስቆጣ እንደሚችል እየተነገረ ነው
በአረብ- እስራኤል ግጭት ምክንያት ግንኙነታቸው ሻክሮ የቆየው እስራኤል እና ሱዳን የሰላም ስምምነት ሊፈራረሙ መሆኑ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡
ሀገራቱ የሰላም ስምምነቱን ለመፈራረም የተስማሙት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን ካርቱምን መጎብኘታቸውንና በቆይታቸው ከሌተናንት-ጀነራል ቡርሃን መምከራቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
እስራኤል ዜጎቿ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ የሚያበረታታ ውሳኔ ልታሳልፍ ነው
ሁለቱ ሀገራት ፊርማቸውን የሚያኖሩበት የመጨረሻ ነው የተባለለት ሰነድ መዘጋጀቱም ነው የተገለጸው፡፡
ለበርካታ ዘመናት ለእስራእል እውቅና ሳትሰጥ የቆየችው ሱዳን እንደፈረንጆቹ 2020 አሜሪካ የተጫወተችውን የአደራዳሪነት ሚና ተከትሎ እውቅና ለመስጠት ቃል መግባቷ አይዘነጋም፡፡
ምንም እንኳን ስምምነቱ እስካሁን ሳይተገበር ቢቆይም፡፡
በአሜሪካ እውቅና በተካሄደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የካርቱም ጉብኝቱ ስምምነቱ ተፈርሞ ወደ ተግባር ወደ ሚለወጥበት ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን "የሱዳን ወታዳረዊ ኃይል የሽግግር ሂደት አካል ሆኖ ለሚቋቋመው የሲቪል መንግስት ስልጣን ካስረከበ በኋላ የፊርማ ስነ ስርአቱ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረሰው የሰላም ስምምነት ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋትን ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተናግረዋል ሚኒስትሩ፡፡
የፊርማው ስነ-ስርአት የሚካነውንው ለስምምነቱ ከፍተኛውን ሚና በተወጣችው ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ እንደሚሆንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
እስራኤል ይህን ትበል እንጅ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ በካርቱም በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ባህሬን እና ሞሮኮ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያሻሻሉ ሀገራት ናቸው፡፡
ግብጽ እንደፈረንጆቹ በ1979 እንዲሁም ጆርዳን በ1994 ላይ ደግሞ ጆርዳን ለእስራኤል እውቅና የሰጡ ሀገራት መሆናቸውም ይታወቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአረቡ ዓለም ሀገራት ከእስራኤል ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ወይም የአብርሃም ስምምነት ተብሎ የሚታወቀውን ሰነድ ለመፈረም እየወሰዱት ያለውን እርምጃ ፍልስጤማውያንን ሊያስቆጣ ይችላል እየተባለ ነው፡፡ምክንያቱም የአረብ ሀገራት ከዚህ ቀደም ለእስረኤል እውቅና የምንሰጥ ከሆነ “መጀመሪያ ሀገሪቱ ከፍልስጤም ጋር ያላትን አለመግባባት መፍታት አለባት” የሚል ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጡ ነበር፡፡
ሳኡዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ኢራቅ እና ሶሪያ አሁንም ድረስ ለእስራኤል እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሀገራት ናቸው፡፡