ዚምባቡዌ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎችን በእስራት እቀጣለሁ አለች
ከሶስት ቀናት በላይ አድማ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች እስከ ስድስት ወራት በሚደርስ እስራት ይቀጣሉ ተብሏል
ፕሬዚዳንት መናንጋዋ የፈረሙት አዲስ ህግ፥ የጤና ባለሙያዎች አድማ ላይ ሆነውም ለድንገተኛ ህመምተኞች አገልግሎት መስጠትን ያስገድዳል
ዚምባቡዌ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎችን በእስራት እቀጣለሁ አለች።
ዚምባቡዌ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎችን በእስራት እንደምትቀጣ አስጠቅቃለች።
የደቡብ አፍሪካዋ ሀገር የተራዘመ የስራ ማቆም አድማን የሚከለክል ህግ ይፋ አድርጋለች።
ፕሬዚዳንት ኢመርሰን መናንጋዋ የፈረሙት አዲስ ህግ፥ ከሶስት ቀናት በላይ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች እስከ ስድስት ወራት በሚደርስ እስራት እንደሚቀጡ ያመላክታል።
አዲሱ ህግ የጤና ባለሙያዎች አድማ ላይ ሆነውም ለድንገተኛ ህመምተኞች አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም ያስገድዳል ነው የተባለው።
ዶክተሮች እና ነርሶችን ጨምሮ አጠቃላይ የጤና ባለሙያዎች ካለባቸው ሃላፊነት አንፃር የስራ ማቆም አድማ ሊመቱ የሚችሉት ለሶስት ቀናት ብቻ መሆኑን የመንግስት ቃል አበባይ ኒክ መናንጋዋ ተናግረዋል።
እንደ ደቡብ አፍሪካና ዛምቢያ ያሉ ሀገራትም የስራ ማቆም አድማ በሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ላይ ከደመወዝ ቅጣት እስከመባረር የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱ ቢያሳስቡም እንደ ሃረሪ እስራትን አልደነገጉም።
በዚምባቡዌ ለሳምንታት የሚዘልቁ የስራ ማቆም አድማዎች የሀገሪቱን የጤና ስርአት አደጋ ላይ ሲጥሉት ይስተዋላል።
የጤና ባለሙያዎቹ በወር በአማካይ የሚከፈላቸው 100 ዶላር መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት እንደማይችል በማንሳት አመፁን ገፍተውበታል።
በአንድ ወቅት በህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና መሰረተ ልማት ግንባታ በአፍሪካ ስሟ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ዚምባቡዌ የጤና ባለሙያዎቿ ወደ ውጭ የሚሰደዱባት ሀገር ሆናለች።