የእስራኤል ጦር ሆስፒታሉ የታጋቾች ማቆያ ሆኖ ማገልገሉን የሚያሳይ ምልክት አገኘሁ አለ
ሀማስ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጸፋ እርምጃ እስካሁን ከ11ሺ በላይ ሰዎች ተገድለዋል
የእስራኤል ጦር በጋዛ በሚገኘው የህጻናት ሆስፒታል ውስጥ የጦር መሳሪያ ተከማችቶበት ነበር ያለውን ቦታ የሚየሳይ ቪዲዮ እና ፎቶ ለቋል
የእስራኤል ጦር ሆስፒታሉ የታጋቾች ማቆያ ሆኖ ማገልገሉን የሚያሳይ ምልክት አገኘሁ አለ።
የእስራኤል ጦር በጋዛ በሚገኘው የህጻናት ሆስፒታል ውስጥ የጦር መሳሪያ ተከማችቶበት ነበር ያለውን ቦታ የሚየሳይ ቪዲዮ እና ፎቶ ለቋል። እንደጦሩ ከሆነ ቦታው ከመሳሪያ ማከማቻነት በተጨማሪ የታጋቾች ማቆያ ሆኖ አገልግሏል።
የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋሪ ወታደሮቹ የእጅ ቦምብ፣ የአጥፍቶ ጠፊ ልብስ እና ሌሎች ፈንጅ የሆኑ ቁሳቁሶችን የያዘ የማዘዣ ጣቢያ በሆስፒታሉ ቤዝመንት ውስጥ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
"ሀማስ ታጋቾችን እዚህ አቆይቷቸው እንደነበር የሚያሳይ ምልክት አግኝተናል" ያሉት ቃል አቀባዩ አሁን ላይ ምርመራ እየደረገ ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ይፋ በተደረገው ቪዲዮ ውስጥ የመኖሪያ ክፍሎችን፣ የምግብ ማብሰያ ቦታዎችን እና ከፍተኛ የሀማስ አዛዥ መኖሪያ ነው የተባለውን ቦታ አሳይተዋል።
ሀማስ በጥቅምት ወር ጥቃት ፈጽሞ ታጋቾችን ይዞ የመጣበት ሳይሆን አይቀርም የተባለ በጥይት የተመታ ሞተርሳይክልም መገኘቱን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
ሀማስ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጸፋ እርምጃ እስካሁን ከ11ሺ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ሀማስ እስራኤል ለአምስት ቀናት የሚቆይ ተኩስ አቁም የምታደርግ ከሆነ በምትኩ 70 ታጋቾችን እንደሚለቅ ተገልጿል።
ሀማስ እስራኤል በእግረኛ ጦር ወደ ጋዛ መግባት ስትጀምር ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም እስራኤል አልተቀበለችውም።
በጦርነቱ በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ በመፍጠሩ ምክንያት ተመድ እና በርካታ ሀገራት የተኩስ አቁም ጥሪ ቢያቀርቡም ሀማስን ለማጥፋት እቅድ የያዘችው እስራአል ፈቃደኛ አልሆነችም።