የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጸጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር በዝግ መክረዋል
በመንግስታቱ ድርጅት የፍልስጤም ልዑክ በእስራኤል እየተፈጸመ ነው ያለውን የሰብዓዊ ወንጀል ለማስቆም የበለጠ እንዲሰሩ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ተማጽኗል።
- እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖስ ነጭ ፎስፈረስ ተጠቅማለች የሚል ክስ ቀረበባት
- እስራኤል ከ1 ሚሊየን በላይ የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች
እስራኤል ግማሹ የጋዛ ሰርጥ ነዋሪ ጥቃት ከሚፈጸምበት አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ተወካይ ሪያድ ማንሱር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአረብ ቡድን አምባሳደሮች ስብሰባ ላይ "የበለጠ ማድረግ አለባቸው [ጉቴሬዝ]። የተደረገው ሁሉ በቂ አይደለም። በሰብዓዊነት ላይ የተጋረጠውን ወንጀል ለማስቆም ሁላችንም የበለጠ ጥረት ማድረግ አለብን" ብለዋል።
አርብ ዕለት ሀገራት እስራኤል ሰሜን ጋዛን ለማጥቃት ከያዘችው አቋም እንድትገታ ጠይቀዋል።
የእስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን በሰሜናዊ ጋዛ ለሚገኙ ነዋሪዎች የተሰጠው ማስጠንቀቂያ "የዜጎችን ጉዳት ለመቅረፍ" ነው ብለዋል።
በርካታ ሀገራት ለጦርነቱ መፍትሄ ነው ያሉትን ምክረ-ሀሳብ ለተመድ በማቅረብ፤ ጦርነት ቆሞ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።
የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 15 አባላት ላሉት የጸጥታው ምክር ቤት በዝግ ገለጻ አድርገዋል።
"በጋዛ ያለው ሁኔታ አደገኛ ሁኔታ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል" ያሉት ጉቴሬዝ፤ ከዚህ የባሰ ቀውስ እንዳይፈጠር በቀጣናው ከመሪዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ገልጸዋል።