የእስራኤል ጦር ሀማስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ከታሰበው በላይ ይንቀው እንደነበር በምርመራ ሪፖርቱ ገለጸ
ምርመራው ሀማስ የደቡብ እስራኤልን ድንበር ጥስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊትና በኃላ የእስራኤል ወታደራዊ ስትራቴጂ፣ የውጊያ ሁኔታና የስለላ ምን ይመስል እንደነበር ተመልክቷል

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ብሔራዊ ምርመራው መደረግ ያለበት ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ነው ሲሉ ነበር
የእስራኤል ጦር ሀማስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ከታሰበው በላይ ይንቀው እንደነበር በምርመራ ሪፖርቱ ገለጸ።
የእስራኤል ጦር ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 በእስራኤል ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ያለውን አቅም ከታሰበው በላይ ይንቀው እንደነበረና "ንጹሃን እስራኤላውያን ከጥቃት የመከላከል ተልዕኮውን አለመወጣቱን" ትናንት የታተመው የእስራኤል ጦር ምርመራ ሪፖርት በማጠቃለያው ገልጿል።
ሀማስ ለአጠቃላይ ጦርነት ፍላጎት የለውም የሚለው ግምት ለረጅም ጊዜ በደንብ ሳይፈተሽ መቅሩቱ የእስራኤል ዝግጅትና ጥቃት የመከላከል አቅም ደካም እንዲሆን አድርጎታል ብሏል ሪፖርቱ።
"ሀማስ የጦርነት ፍላጎቱን በሚቀንሱ ጫናዎች ተጽዕኖ ያድርበታል የሚል እምነት ነበር" ሲል ሪፖርቱ ጠቅሷል። ምርመራው ሀማስ የደቡብ እስራኤልን ድንበር ጥስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊትና በኃላ የእስራኤል ወታደራዊ ስትራቴጂ፣ የውጊያ ሁኔታና የስለላ ምን ይመስል እንደነበር ተመልክቷል።
እንደጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ እስራኤል ሀማስ ያደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ በጋዛ በፈጸመችው መጠነሰፊ ጥቃት 48 ሺ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። አብዛኛው የጋዛ ክፍል ወደ ፍርስራሽ መቀየሩንና 2.3 ከሚሆነው የጋዛ ነዋሪ አብዛኞቹ ለበርካታ ጊዜ መፈናቀላቸውን የሰብዓዊ መብት ተቋመት ተናግረዋል። በጦርነቱ 400 የእስራኤል ወታደሮችም ተገድለዋል።
የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሲቪል ድርጅቶች በዘመናዊ እስራኤል ታሪክ ትልቅ ውድቀት እንዲፈጠር ባደረገው የመንግስት ድክመት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጫና ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ምርመራው የተካሄደው።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ብሔራዊ ምርመራው መደረግ ያለበት ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ነው ሲሉ ነበር።
እስራኤልና ሀማስ ባለፈው ወር የደረሱት 15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ያስቆመው የመጀመሪያ ዙር የተኩስ ኡቀም ስምምነት ከሁለት ቀናት በኋላ ያበቃል።
እንደሪፖርቱ ከሆነ እስራኤል በስለላና እንደ ሄዝቦላ ባሉ ቡድኖች ላይ ትኩረት አድርጋ ስለነበረ ባላሰበችው ሰአት ተጠቅታለች ብሏል። ወታደራዊ አዛዦች የጥቅምቱን ጥቃት የሚያመላክት ነገር ባለማግኘታቸው ድንበር ለመጠበቅ ወታደር አላሰማሩም። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የጦሩ የምርመራ ውጤቱ እንዳልደረሳቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል።