
ትራምፕ ከዚህ ከቀደም ፕሬዝዳንት ዘለንስኪን “ውጤታማ ኮሜዲያን እና አምባገነን” ብለው ወርፈው ነበር
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም “አምባገነን” ሲሉ የተቿቸውን የዩክሬኑ አቸቻቸው ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ጀግና መሪ ነው” ሰሊ አሞካሽተዋል።
ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው አለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ከሚኖራቸው ውይይት አስቀድመው በዋይት ኃውስ በሰጡት አስተያየት፤ “ለቮሊድሚር ዘለንስኪ ትልቅ ክብር አለኝ” ብለዋል።
በቅርቡ ዘለንስኪን “አምባገነን” ብለው በመጥራታቸው ይቅርታ እንደሚጠይቁ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ትራምፕ “ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ” ነው ሰሊ አሞካሽተዋል።
በዛሬው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ ጥሩ ውይይት እንደሚኖራቸው የገመቱት ትራምፕ፤ በዩክሬን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እና በፍጥነት እየሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና በዩክሬን ውድ ማዕድናት ዙሪያ ስምምነት ለመፈራረም ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን እንዲሁም “ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።
“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።
“ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም” ብለውም ነበር ትራምፕ።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ ውስጥ እየኖሩ ወይንም በሀሰት መረጃ እየተነዱ ነው” ማለታውም አይዘነጋም።