በእስራኤል-ሄዝቦላህ ግጭት፤ ቤሩትና ሌሎች የሊባኖስ ከተሞች ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
በእስራኤል የአየር ድብደባ እስካሁን ከ1 ሺህ በላይ ሊባኖሳውያን ተገድለዋል
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በእስራኤል የሚፈጽመውን ጥቃት እንደሚያጠናክር ዝቷል
በእስራኤል እና በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው የሄዝቦላህ ቡድን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት እያገረገሸ እና መጠነ ሰፊ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል።
በያዝነው ሳምንት ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ በሚገኙ የሄዝቦላህ ይዞታዎች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ እየፈጸፈመች ሲሆን፤ ሄዞቦላህም ከዚህ ቀደም ጥቅም አውሎ የማያውቀውን ሚሳኤል በመጠቀም እስከ ማእካላዊ እስራኤል ድረስ እያሰወነጨፈ ይገኛል።
እስራኤል በሊባኖስ የምትፈጽመው ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፤ ከቤሩት 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ናባቲህ ከተማ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአየር ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።
በእስራኤል የአየር ድብደባ እስካሁን 1 ሺህ 300 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ700 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አር.ቲ የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴርን ዋቢ አደርጎ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በደቡባዊ ሊባኖስ በነበረ ከባድ ፍንዳታ የ87 ዓመት ፈረንሳያዊት ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
በተያያዘ በኢራቅ ውስጥ የሚንቀሳቀው እስላማዊ ቡድን በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቀ ሲሆን፤ ቡድኑ በጎላን ከፍታ አካባቢ በሚገኝ ኢላማ ላይ በድሮን ጥቃት ፈጽሜያለሁ ብሏል።
በኢራን የሚደገፈው የኢራቁ ታጣቂ ቡድን በጎላን ከፍታ ላይ ቁልፍ ኢላማዎችን አጥቅቻለሁ በሊም፤ ከእስራኤል በኩል እስካሁን ምንም አልተባለም።
በሊባኖስ የመገናኛ መሳርያዎች ላይ የተገጠሙ ፈንጂዎችን በማፈንዳት ጥቃት ማድረስ የጀመረችው እስራኤል ከሰኞ ጀምሮ መጠኑ ከፍ ያለ የአየር እና የሚሳኤል ጥቃት በሊባስ ላይ እየፈጸመች ትገኛለች።
ሄዝቦላህ ለእስራኤል እየሰጠ በሚገኝው ምላሽ እስከዛሬ በቡድኑ ጥቅም ላይ ውለው የማያውቁ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ጭምር በመጠቀም በማዕከላዊ እስራኤል ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።
ይህን ተከትሎም ቀጠናው ከአስርተ አመታት ወዲህ ወደ አከባቢያዊ ጦርነት የማምራት እድሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመሆኑ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ምዕራባውያን ሁለቱ ወገኖች ውጥረቱን እንዲያረግቡ ተደጋጋሚ ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው።
አሜሪካ እና አጋሮቿ በሄዝቦላህ እና እስራኤል መካከል የ21 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ያቀረቡትን ጥያቄ የኔታንያሁ መንግስት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱ ጦር ኢታማዦር ሹም በሊባኖስ የምድር ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሀገሪቱ ጦር እንዲዘጋጅ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል።
ኢታማዦር ሹሙ ሄርዚ ሃሊቪ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ድንበር ተገኝተው በአካባቢው ለሚገኙ የጦር አባላት ባደረጉት ንግግር የአየር ሀይሉ እየፈጸመ ያለው ጥቃት ለእግረኛ ጦሩ መደላደሎችን ለመፍጠር ነው ማለታቸው ተሰምቷል።
የእስራኤል ጥቃት በመላው ሊባኖስ ከፍተኛ ስጋትን እና ውጥረትን የፈጠረ ሲሆን፤ በደቡብ እና ምስራቅ ሊባኖስ ውስጥ የሚኖሩ በርካቶችም መኖሪያቸውን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከዚህ ቀደም በቴሌቪዥን በተሰራጨ መግለጫ ላይ፤ “እኛ ችግርራችን ከሄዝቦላህ ጋር ነው ያሉ ሲሆን፤ ሊባኖሳውያን ግጭት ካለበት አካባቢ ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስበዋል።
እስራኤል-ሄዝቦላህ ግጭት ሰለባ የሆኑት አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?
እስራኤል ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸመችበት ካለው አካባቢ ውስጥ ደቡብ እና ምስራቅ ሊባኖስ ዋነኛው ሲሆን፤ በደቡባዊ ቤሩት፣ ቢንት ጀቢል፣ ሃሪስ፣ ባልቤክ፣ ካፋር ሃታ፣ አረብ ሳሊም፣ ታራያ፣ ሁላ፣ ቶውራ እና ሌሎችም አካባቢዎች ይገኙበታል።
እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በሊባኖስ ዋና ከተማ በሆነችው ደቡባዊ ቤሩት ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ የሂዝቦላህ ወታራዊ አዛዥ ኢብራሂም አቂልን መግደሏ ይታወሳል።