እስራኤል የተመድ ዋና ጸኃፊ ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እግድ ጣለች
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቁት የተመድ ዋና ጸኃፊ ኢራን በእስራኤል የፈጸመችውን ጥቃት "በግልጽ" ባለማውገዛቸው ምክንያት ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እግድ ጥለውባቸዋል
ኢራን ትናንት ምሽት ከ180 በላይ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋች
እስራኤል የተመድ ዋና ጸኃፊ ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እግድ ጣለች።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው እለት እንዳስታወቁት የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒየ ጉተሬዝ ኢራን በእስራኤል የፈጸመችውን ጥቃት "በግልጽ" ባለማውገዛቸው ምክንያት ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እግድ ጥለውባቸዋል።
በሊባኖስ በሚገኘው አጋሯ እና በእስራኤል መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ኢራን ትናንት ምሽት ከ180 በላይ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች። ከተወነጨፉት ሚሳይሎች ውስጥ አብዛኞቹ አየር ላይ የከሸፉ ቢሆንም የተወረኑት ግን የአየር መከላከያ ስርአቱን ማለፍ ችለዋል።
ጉተሬዝ በትናንትናው እለት አዲሱ "የመካከለኛው ምስራቅ ጥቃት" ውጥረት የሚጨምር ነው ሲሉ አውግዘውታል። ጉተሬዝ ኢራን የሰነዘረችውን ጥቃት በግልጽ አልጠቀሱም።
ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሊባኖስ በእግረኛ ጦር ጥቃት የጀመረችው እስራኤል በድንበር አካባቢ ከሄዝቦላ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደች መሆኗንም ገልጻ ነበር።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንዳሉት ጉተሬዝ የኢራንን ጥቃት በግልጽ ማውገዝ ባለመቻላቸው ወደ እስራኤል እንዳይጠቡ ታግደዋል።
"ሁሉም የአለም ሀገራት በሚባል ደረጃ ያወገዙትን የኢራን ሰይጣናዊ ጥቃት ያላወገዘ የእስራኤልን ምድር መርገጥ አይገባውም"ብለዋል ካትዝ።
"አይንቶኒ ጉተሬዝም ይሁን ሌላ እስራኤል ዜጎቿን እና ብሔራዊ ክብሯን መከላከሏን ትቀጥላለች።"
ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ያደረሰችው የሀማስ እና ሄዝቦላ መሪዎች ግድያን እና በሊባኖስ ላይ ያደረገችውን ወረረ ለመበቀል ነው።
ጥቃቱን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ኔታንያሁ "ኢራን ትልቅ ስህተት ሰርታለች፤ ዋጋ ትከፈላለች"ሲሉ ዝተዋል።
አሜሪካ በበኩሏ በኢራን ላይ የአፈጸፋ እርምጃ ለመውሰድ ከእስራኤል ጋር እየሰራች መሆኗን ገልጻለች።