እስራኤል በጋዛ ተኩስ ጀመረች
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥቃቱን በመጀመር እስራኤል ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራች ነው ብለዋል
እስራኤል ሮኬት በማስወንጨፍ ስምምነቱን ጥሷል ስትል ሀማስን ከሳለች
እስራኤል በድጋሚ በጋዛ ተኩስ ጀመረች።
ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ሀማስን የከሰሰችው እስራኤል በጋዛ የማጥቃት ዘመቻ መጀመሯን እና ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
እስራኤል ሮኬት በማስወንጨፍ ስምምነቱን ጥሷል ስትል ሀማስን ከሳለች።
በፈረንጆቹ ጥቅምት 24 በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው ጦርነቱን በጊዜያዊነት ጋብ የማድረግ ስምምነት ለሁለት ጊዜ በመራዘሙ በርካታ እስራኤላውያን ታጋቾች እና ፍልስጤማውያን እስረኞች እንዲለቀቁ አስችሏል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሊጠናቀቅ አንድ ሰአት ገደማ ሲቀረው የተተኮሰ ሮኬት መትታ መጣሏን እስራኤል ገልጻለች። በዚህ ጉዳይ ሀማስ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጊዜ ገደቡ ካለቀ በኋላ እስራኤል የራፋ ድንበር ሟቋረጫን ጨምሮ በጋዛ ላይ የከባድ መሳሪያ እና የአየር ድብደባ ማድረሷን የፍልስጤም ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በደቡብዊ ጋዛ በሚገኘው ካን ዮኒስ የከባድ መሳሪያ ድምጽ እንደሚሰማ እና ጭስ ወደ አየር ሲወጣ መታየቱን ሮይተርስ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የእስራኤል ጦርም በጋዛ የሚገኙ የሀማስ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጧል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥቃቱን በመጀመር እስራኤል ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራች ነው ብለዋል።
እስራኤል ባለፈው ጥቅምት ወር ድንበራን ጥሶ 1200 ዜጎቿን የገደለባትን እና 240 ያገተባትን ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ማቀዷ ይታወሳል።