እስራኤል በውጊያ ላይ ከሞቱ ወታደሮች የወንድ ዘር ፍሬ መሰብሰቧን አስታወቀች
ከሀማስ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት የሞቱ 91 ወታደሮች የዘር ፍሬያቸው ተሰብስቧል
ህይወታቸው ያለፉ ወታደሮች የዘር ፍሬያቸው የሚሰበሰበው ራሳቸውን እንዲተኩ ለማድረግ ነው ተብሏል
እስራኤል በውጊያ ላይ ከሞቱ ወታደሮች የወንድ ዘር ፍሬ መሰብሰቧን አስታወቀች፡፡
ከአራት ወር በፊት የተጀመረው የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ከ27 ሺህ በላይ ፍለስጤማዊያን ሲገደሉ እስካሁን ቁጥሩ ያልተወቁ የእስራኤል ወታደሮችም ተገድለዋል፡፡
የእስራኤል መንግስት ወደ ፍልስጤም የላካቸው ወታደሮች በሐማስ እየተገደሉበት ሲሆን ከሞቱ ወታደሮች የወንድ የዘር ፍሬያቸውን መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡
እንደ ጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ ከሆነ የ91 ወታደሮች የዘር ፍሬ በቤተሰባቸው እና ሚስቶቻቸው ወይም ፍቅረኞቻቸው ፈቃድ መሰረት የዘር ፍሬያቸው በሳይንሳዊ መንገድ ተሰብስቧል፡፡
የተሰበሰበው ይህ የዘር ፍሬ ልጅ እንዲወልዱ አልያም ልጅ የመውለድ ፍላጎት ላላቸው ሴቶች ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
የእስራኤል የህክምና ባለሙያዎች ከሀማስ ጋር ሲዋጉ ህይወታቸው ያለፈ ወታደሮችን የዘር ፍሬ የሚሰበስበው ህይወታቸው ባለፈ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሃማስ፥ እስራኤል “የፍልስጤሙን ማንዴላ” ከእስር እንድትለቅ ጠየቀ
ፍቅረኛ አልያም ሚስት የሌላቸው በውጊያ ላይ የሞቱ ወታደሮችን የዘር ፍሬ በቅርብ ቤተሰባቸው ፈቃድ መሰረት የሚሰበሰብ ሲሆን ፈቃደኛ ለሆኑ ወይም የወንድ የዘር ፍሬ ለሚፈልጉ ሴቶች ይለገሳልም ተብሏል፡፡
የእስራኤል ሐማስ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ ቢሆኑም ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲኖር በእስራኤል ላይ የሚደረገው ጫና እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
የዓለማችን 35 በመቶ ንግድ መስመር የሆነው ቀይ ባህር በዚሁ ጦርነት ምክንያት የስጋት ቀጠና የሆነ ሲሆን ዓለም አቀፍ መርከቦችም በስጋት ምክንያት ጉዟቸውን እየሰረዙ ናቸው፡፡
በቀይ ባሕር ትራንስፖርት ተጠቃሚ ከሆኑ ሀገራት መካከል ግብጽ ከስዊዝ ካናል የምታገኘው ገቢ በ46 በመቶ ቀንሶብኛል ማለቷ ይታወሳል፡፡