ሜጀር ጀነራል ዮራን ፍንቅልማን "የእስራኤል ጦር በአስርት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዛ መሀል ላይ እየተዋጋ ነው" ብለዋል
የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ መሀል ላይ ውጊያ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ።
የእስራል መከላከያ ኃይል እንዳስታወቀው የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ከተማ እምብርት ዘልቆ ገብቷል።
ሜጀር ጀነራል ዮራን ፍንቅልማን "የእስራኤል ጦር በአስርት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዛ መሀል ላይ እየተዋጋ ነው።" ብለዋል።
በከተማዋ ዙሪያ የታንክ ከበባ በማድረግ ነው ጦሩ ወደ መሀል ከተማው ዘልቆ ሊገባ የቻለው።
"በየቀኑ እና በየሰአቱ ጦሩ ታጣቂዎችኝ እየገለ፣ ዋሻዎችን እየገለጠ እና እያወደመ ጠላት ወደአለበት ማዕከል የሚያደርገውን ግስጋሴ መቀጠሉን" ሜጀር ጀነራሉ ተናግረዋል።
የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ በበኩሉ ጠላት ባላቸው የእስራኤል ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ይገልጻል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የሀማስ መሰረተልማቶች፣ አዛዦች፣ መደበቂያቸው እና የግንኙነት ቦታቸው የጦሩ የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የጦሩ ዋና ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሀጋሪ የእስራኤል ጦር የምህንድስና ክፍል አባላት የሀማስን የመሬት ውስጥ ዋሻዎች ለማፈራረስ ፈንጅዎችን እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል።
የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት 2.3 ህዝብ በሚኖርባት የጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ አስከትሏል።
የአረብ ሀገራት በጋዛ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቁም ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት ያለመችው እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ አልተቀበሉትም።