እስራኤል እና ሀማስ አዲስ ስምምነት ላይ ደረሱ
በጋዛ በሀማስ እጅ እንዳሉ የሚገመቱት 100 ታጋቾች ቤተሰቦች መድሃኒት ለታጋቾች እንዲላክላቸው ሲወተውቱ ቆይተዋል
እስራኤል እና ሀማስ ለታጋቾች መድሃኒት እና እርዳታ እንዲገባላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኳታር ገልጻለች
እስራኤል እና ሀማስ አዲስ ስምምነት ላይ ደረሱ።
እስራኤል እና ሀማስ ለታጋቾች መድሃኒት እና እርዳታ እንዲገባላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኳታር ገልጻለች።
ኳታር እንዳለችው በጋዛ ለሚገኙት ታጋቾች መድሃኒት እንዲደርሳቸው እና በምትኩ ለፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች እርዳታ እንዲደርሳቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል።
መድሃኒት እና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታዎች ለፍልስጤማውያን የሚደርስ ሲሆን በጋዛ ለሚገኙት ታጋቾች ደግሞ መድሃኒት እንደሚደርሳቸው እንደሚደረግ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤክስ ላይ በፖሰተው መግለጫ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ አክሎ እንገለጸው መድሃኒቱ እና እርዳታው በዛሬው እለት ከዶሃ ወጥቶ ወደ ግብጽ ተጓጉዞ ወደ ጋዛ እንደሚገባ ይደረጋል።
በጋዛ በሀማስ እጅ እንዳሉ የሚገመቱት 100 ታጋቾች ቤተሰቦች መድሃኒት ለታጋቾች እንዲላክላቸው ሲወተውቱ ቆይተዋል።
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 1200 ሰዎችን ገድሎ እና 240 ሰዎችን ማገቱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ሶስት ወራትን አስቆጥሯል።
ከታገቱት ወስጥ 1/3 የሚሆኑት ከባድ ህመም እንዳለባቸው እና መድሃኒት እንደሚፈልጉ 'የሆስቴጅ እና ሚሲኔግ ፋሚሊስ ፎረም' ገልጿል።
ባለፈው ህዳር ወር በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው የስድስት ቀን ተኩስ አቁም ካበቃ በኋላ እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላች።
ሀማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ባለው መጠነሰፊ ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 24ሺ በላይ ሆኗል።
እንደሚኒስቴሩ ከሆነ ከተገደሉት ውስጥ 10ሺ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው።