በቱርክ ታስሮ የነበረው እስራኤላዊ እግር ኳስ ተጨዋች ወደ ሀገሩ ተመለሰ
የተጨዋቹ መታሰር እስራኤል እና ቱርክ የቃላት ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል
እዝቅኤል ከጨዋታው በኋላ በቱርኳ ደቡባዊ ከተማ ግጭት አነሳስቷል በሚል ለአጭር ጊዜ በፖሊስ ታስሮ ነበር
በቱርክ ታስሮ የነበረው እስራኤላዊ እግር ኳስ ተጨዋች ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
በቱርክ ታስሮ የነበረው ሳጊቭ እስቅኤል የተባለው እስራኤላዊ እግር ኳስ ተጨዋች ወደ ሀገሩ እስራኤል ተመልሷል።
በቱርክ ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደ ጨዋታ ላይ በፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ለታገቱት እስራኤላውያን አጋርነቱን ያሳየው ተጨዋች ውዝግቡ አስነስቶ ነበር።
እዝቅኤል ከጨዋታው በኋላ በቱርኳ ደቡባዊ ከተማ ግጭት አነሳስቷል በሚል ለአጭር ጊዜ በፖሊስ ታስሮ ነበር።
ተጨዋቹ ተመልሶ ወደ ቱርክ ቢሄድ ይከሰስ ወይም አይከሰስ አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
እዝቅኤል በእጁ ላይ ባሰረው ፋሻ ላይ የእስራኤል ታጋቾችን የሚደግፍ መልእክት ማስተላለፉን ተከትሎ በአንታሊያስፖር ታግዶ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል።
ተጨዋቹ በፋሻው ላይ "100 ቀናት፣7/10" በማለት የታገቱት እስራኤላውያን 100 ቀናት እንደሞላቸው መልእክት አስተላለልፏል።
ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ሀማስ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት በማድረስ ነበር 1200 ሰዎችን ገድሎ፣ ሌሎች 240 የሚሆኑ ደግሞ አግቶ ወደ ጋዛ የወሰዳቸው።
በህዳር መጨረሻ አካባቢ በኳታር አደራዳሪነት የተካሄደው የተኩስ አቁም ስምምነት 100 የሚሆኑ ታጋቾች በሀማስ እጅ እንዳሉ ከስድስት ቀናት በኋላ መጣሱ ይታወሳል።
ተጨዋቹ ማንምም ለመተንኮስ እንዳልፈለገ እና ይልቁንም ጦርነት እንዲቆም መፈለጉን ለፖሊስ መግለጹን የቱርክ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የተጨዋቹ መታሰር እስራኤል እና ቱርክ የቃላት ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን አማካሪ ተጨዋቹን "የእግር ኳስ ማለያ የለበሰ የእስራኤል ተናካሽ ውሻ" ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ቱርክ በተጨዋቹ ላይ የፈጸመችውን ድርጊት ኮንነዋል።
ተጨዋቹ የታሰረው እስራኤል እና ቱርክ በጋዛ የተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ግንኙነታቸው ወደ ዲፕሎማሲያዊ ግጭት ከፍ ባለበት ወቅት ነው።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ጣይፕ ኢርዶጋን እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል እየፈጸመች ነው፤ በአለምአቀፉ ፍርድ ቤት መከሰስ አለባት ማለታቸው ይታወሳል።