ሀገሪቱ ጋዛን በቦንብ በመደብደብ በሰጠችው አጻፋ ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል
እስራኤል ሀማስን ከምድረገጽ እንደምታጠፋ ገለጸች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የሀማስን ጦርነት ለመምራት ዕረቡ ዕለት አስቸኳይ መንግስት አቋቁመዋል።
የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር ባለፈው ቅዳሜ ለደረሰው ጥቃት የፍልስጤሙን ታጣቂ ቡድን ሀማስን ከምድር ገጽ እንደሚያጠፉ ቃል ገብተዋል።
ሀማስ ባደረሰው ጥቃት የሟቾች ቁጥር አንድ ሽህ 200 የደረሰ ሲሆን፤ ጥቃቱ በእስራኤል ታሪክ በፍልስጤም የደረሰ እጅግ ገዳዩ ነው ተብሏል።
ለጥቃቱ እስራኤል ጋዛን በቦንብ በመደብደብ በሰጠችው አጻፋ ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ኔታኒያሁና ተቃዋሚ ፓርቲው በጋራ በሰጡት መግለጫ አስቸኳይ መንግስት ለማቋቋም ተስማምተዋል።
ለእስራኤል ህልውና ሲባል ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማለት ሀማስን ለመዋጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ክፉ ጠላት እንደገጠማቸው ጠቅሰዋል።
የእስራኤል የመከላከያ አዛዥ እና ጄኔራል የነበሩት ተቃዋሚ ቤኒ ጋንትዝ አንድ ላይ ሆነን የምናሸነፍበት ጊዜ ነው ብለዋል።
"ለሰላም ጊዜ አለው፤ ለጦርነትም ጊዜ አለው። አሁን የጦርነት ጊዜ ነው" በማለት የትኩረታቸውን አቅጣጫ አስረግጠው ተናግረዋል።