በጋዛ ውስጥ የሚገኙት ግዙፎቹ የኢንዶኔዤያን እና የቱርክ ወዳጅነት ሆስፒታሎ ስራ አቁመዋል
ሃማስ እስራኤል ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬ 27ኛ ቀኑን ይዟል።
እስራኤል ወደ ሁለተኛ ምእራፍ ተሸጋግሯል ባለችው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በእግረኛ ጦር፣ በብረት ለበስ እና በአየር አጠናክራ ቀጥላለች።
ሃማስም ወደ እስራኤል ሮክት መረኮሱን የቀጠለ ሲሆን፤ በምድርም ታጣቂዎች በመሬት ላይም ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ መሆኑን አስታውቋል።
በ27ኛ ቀን የተስተናገዱ ክስተቶች በጥቂቱ
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ አድሯል፤ በጀባሊያ የስደተኞች ካምፕ በተፈጸመ የአየር ድብደባ 195 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።
በአየር ድብደባው 777 ሰዎች ደግሞ ቆስልዋል፤ 120 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የገቡበት አይታወቅም።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ካምፕ ላይ የተፈፈጸመው ጥቃት ጦር ወንጀል ነው ብሏል።
በጋዛ ሰርጥ ሆስፒታሎች ኢላማ መደረጋቸው ቀጥለዋል፤ ይህንን በሰሜን ጋዛ የሚገኘው የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ስራ ለማቆም መገደዱ ተነግሯል።
የቱርክ-ፍልስጤም ወዳጅነት ሆስፒታል ከባድ የአየር ጥቃቶች ተፈጽመውበታል፤ በጋዛ ብቸኛ የካንሰር ሀግክምና ማእከል የሆነው ሆስፒታለ፤ በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራ አቁሟል።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስራኤል በእግረኛ ጦር፣ በብረት ለበስ እና በአየር አጠናክራ ቀጥላለች፤ የእስራኤል ታንኮች ወደ ጋዛ ከተማ ዘልቀው ለመግባት ሞክረዋል።
ሃማስ የፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን፣ ፈንጂዎችን እና የተለያዩ ቦምቦችን ወደ እስራኤል ጦር መተኮሱ እና መወርወሩ ታውቋል።
እስራኤል ከሃማስ ለተፈጸሙባት ጥቃቶች በመድፍና በታንክ ተኩሶች፣ ከሂሊኮፕተር ላይ እንዲሆም ከጦር መርከብ ላይ ሚሳዔሎችን በመተኮስ ምላሽ ሰጥቻ፤ሁ ብላለች።
እስራኤል በጀመረችው የምድር ውጊያ የተገደሉ ወታደሮች ቁጥር 17 መድረሱን አስታውቃለች።
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ የእስረኤልን ድሮን መትቼ ጣልኩ ያለ ሲሆን፤ እስራኤል ድሮኑ መመታን አስተባብላለች።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጻፋ እርምጃም ከ8 ሺህ 8055 በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት መቀጠፉን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሞቱ ሰዎች መካከልም ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት፤ 2 ሺህ ደግሞ ሴቶች ናቸው ሲሆኑ፤ ከ20 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ቆስለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር በጋዛ በየቀኑ ከ420 በላይ ህጻናት ይገደላሉ ወይም ይቆስላሉ ሲሉ አስታውቀዋል።
በእስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 400 ላይ ቆሟል።