በጋዛ አሁንም ሆስፒታሎች የጥቃት ኢላማ መሆናቸው ተጥሏል
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 42ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
እስራኤልም ራሷን ለመከላከልና የአጸፋ እርምጅ ለመውሰድ ጋዛ ላይ ድብደባ ከጀመረች 42 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፤ በእስራኤል ጦርና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል የተቀከቀሰው ጦርነትን እንደቀጠለ ይገኛል።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረ ሲሆን፤ በጋዛ በምድር ስር የሚገኙ ሁለት ስፍራዎችን ማውደሙንም አስታውቋል።
በአየር ድብደባውም በሃማስ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱንም ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።
በጋዛ ውስየጥ የሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች በሃማስ ታግታ የነበረች ዮዲት ውይስ የተባለች እስራኤላዊት አስክሬን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
በጋዛ ከሃን ዩኒስ አካባቢ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው በመውጣት ወደ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲያመሩ የእስራኤል ጦር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
በጋዛ ሙሉ በሙሉ የሞባይል ስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የፍሊስጤም የጤማ ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን፤ ችግሩ የተከሰተው በነዳጅ እጥረት ነው ብሏል።
የጋዛ አል-ሺፋ የመጠጥ ውሃ እና ኦክሲጂን እንደጨረሰ የሆስፒታሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፤ በሆስፒታሉ የሚገኙ ታማሚዎች በውሃ ጥም እየተሰቃዩና እየጮሁ ነው ብለዋል።
በእስራኤል የአየር ድብደባ የተገደሉ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 500ገደማ ከየደረሰ ሲሆን፤ እነዚህም ከ4 ሺህ በላይ ህጻናት መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ የተገደሉ የሰባዓዊ ሰራተኞቹ ቁጥር ከ100 ማለፉን እና ይህም በታሪክ በአንድ ገጭት ላይ የተገደሉ ከፍተኛ የሰራተኞቹ ቁጥር መሆኑን አስታውቋል።
በእስራኤል በሃማስ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥርን 1 ሺህ 400 ወደ 1 ሺህ 200 ዝቅ አድርጋለች። ከ200 በላይ ሰዎች ገድሞ በሃማስ እንደታገቱ ይገኛሉ።