43ኛ ቀኑን በያዘውና አሁንም በቀጠለው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ዙሪያ እስካሁን የምናውቀው?
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርሰው ጥቃት ለተከታታይ 43ኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል
12 ሺህ ፍሊስጤማውያን የሞቱ ሲሆን፣ ከእነዚህም 8300 ሴቶችና ህጻናት ናቸው
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬ 43ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርሰው ጥቃት ለተከታታይ 43ኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ አድሯል።
የእስራኤል ጦር የጋዛ ወደብን መቆጣጠሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ በስፍራው ለፍሊስጤማውያን መታሰቢያ የቆመ ሃውልትን አፍርሷል።
አል ሺፋ ሆስፒታልን የተቆጣጠረችው እስራኤል፣ በሆስፒታሉ ውድጥ ያለከ ታካሚዎቸረ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ እያስገደደች ነው።
እስራኤል ሆስፒታለከን መያዟን ተክትሎ ከሆስፒታሉ እና ከአካ ካቢው እንዲለቁ የተደረጉ 7000 ሰዎች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተብሏል።
ከአል ሺፋ ሆስፒታል የተፈናቀሉ 650 ታማሚዎች እና 7000 ያክል ነዋሪዎች በመንግስት ሚዲያ ህንጻ ውስጥ ተጠልለዋል።
ተፈናቃዮቹ ምግብ፣ የመጠት ውሃ እንዲሹን የህጣናት ወተት አለመኖር ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥሏል።
የእስራኤል ሄሊኮፕተሮች እና የጦር ጄቶች ጋዛን መደብደባቸውን ቀጥለዋል፣ በዚህም የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፣ በርካቶችም ቆስለዋል።
የሃማስ አል ቃሲም ብርጌድ በፍተሻ ጣቢያ ላይ 1 የእስራኤል ወታደር ሞትና ሌሎች አራት መታደሮችን ያቆሰለውን ጥቃት እኔ ነኝ የፈጸምኩት ብሏል።
በተጨማሪም ሃማስ 21 የእስራኤል ጦር ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ እና በከፊል አውድሜያለሁ ሲል አስታውቋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሞትና ሰብዓዊ ቀውስ
እስራኤል በጋዛ እያካሄገችው ያልተቋረጠ የአየር ድብደባ ተከትሎ በጋዛ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር ከ12 ሺህ ያለፈ ሲሆን ከ30 ሺህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሞቱ ፍሊስጤማውያን መካከል 8 ሺህ 300 ያህሉ ህጻናትና ሴቶች ናቸው።
በእስራኤል የሃማስጥን ጥቃት ተከትሊ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 400 ወደ 1 ሺህ 200 ዝቅ ያደረገች ሲሆን፣ 200 ሰዎች አሁንም በሃማስ እንደታገቱ ነው።