31ኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል ሃመስ ጦርነት ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?
በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 10 ሺህ ገደማ ደርሷል
ሃማሰ ጦርነቱ ከተመጀረ ወዲህ እስካሁን ከ8 ሺህ በላይ ሮኬት ወደ እስራኤል ተኩሷል
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 31ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
እስራኤልም ራሷን ለመከላከልና የአጸፋ እርምጅ ለመውሰድ ጋዛ ላይ ድብደባ ከጀመረች 31 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፤ በእስራኤል ጦርና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል የተቀከቀሰው ጦርነትን እንደቀጠለ ይገኛል።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረ ሲሆን፤ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ግዙፍ የተባለለት የአየር ድብደባ በጋዛ ላይ ፈጽማለች።
የእስራኤል መከላከያ ሃይል ጋዛን እንደከበበ ይገኛል።
የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች ከሰሜን ጋዛ ወደ ደቡብ ጋዛ እንዲወጡ ለሰዓታት ተኩስ በማቆም መተላለፊያ መክፈቱን ስታውቋል።
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስራኤል በማእከላዊ ጋዛ በሚገኝ የተፈናቀቃዮች ካምፕ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ በትንሹ 47 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
ሃማስ ወደ እስራኤል ሮኬት መተኮሱን የቀጠለ ሲሆን አዳሩን በርካታ ሮኬቶችን ወደ ማከላዊ እስራኤልና ቴል አቪቭ ከተማ መተኮሱን ቀጥሏል።
ሃማስ ሮኬቶቹን ወደ እስራኤል መተኩሱን የቀጠልኩት የእስራኤል የአየር ድብደባ ባለመቆሙ ነው ብሏል።
የእስራኤል ጦር ለሮኬት ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ስፍራዎችን በካርታ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ወደ ቦምብ መጠለያ ምሽግ ገብተዋል።
ሃማስ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በላፉት 31 ቀናት ከ8 ሺህ በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሷል።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የምድር ወረራ ከጀመረ ወዲህ የሞቱ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 30 ደርሰዋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
በእስራኤል የአየር ድብደባ የተገደሉ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 10 ሺህ ገደማ ከየደረሰ ሲሆን፤ ከ32 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሞቱ ሰዎች መካከልም ከ4 ሺህ በላይ ህጻናት፤ 2 ሺህ ደግሞ ሴቶች ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ የተገደሉ የሰባዓዊ ሰራተኞቹ ቁጥር 88 መድረሱን እና ይህም በታሪክ በአንድ ገጭት ላይ የተገደሉ ከፍተኛ የሰራተኞቹ ቁጥር መሆኑን አስታውቋል።
በእስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 400 ላይ ቆሟል።