በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ባለፉት 24 ሰዓታት ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል? የምናውቀው…
የእስራኤል ጦር በሀገሪቱ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ያቀናበረውን ከፍተኛ የሃማስ ኮማንደር ገደልኩ አለ
ሃማስ በእስራኤል የአየር ድብደባ ካገታቸው ሰዎች መካከል 50 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል
ከ20 ቀናት በፊት ለፍስልጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡
እስካሁን የዓለም ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ የሆነው ይህ ጦርነት መቋጫ ያልተገኘለት ሲሆን በየዕለቱ አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ እና ሰዎች እየተገደሉ እንደሆነ ተገልጿል።
ጦርነቱ ምን ላይ ይገኛል?
የእስራኤል መከላከያ ሃልይል ሌሊቱን በፈጸማቸው ጥቃቶች የሃማስን ከፍተኛ ኮማንደር መግደሉን አስውቋል፤ የተገደለው ኮማንደር የመስከረም 27ቱን ጥቃት በማቀናበር ውስጥ እጁ ነበረበት ተብሏል።
እስራኤል ባለፉት 24 ሰዓታት በጋዛ ውስጥ በርካታ የጋዛ ኢላማዎች ላይ ድብደባ መፈጸሟን አስታውቃለች።
ሃማስ በእስራኤል የአየር ድብደባ ካገታቸው ሰዎች መካከል 50 ያክሉ መገደላቸውን አስታውቋል።
ቤኒ ጋንዝ እና ሌሎችም የእስራዔል የጦርነት ጊዜ ንግስት ካቢኔ አባላት፤ ሀገገሪቱ በጋዛ ውስጥ እያካሄደችው ስላለው ጦርነት ፍላጎቷን በሚያስጠብቅ መልኩየራሷን ውሳኔ እንደምታሰሳልፍ እና በደቡባው ሁኔታ ያለውን ደህንንነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ዓመታትን ሊወስድ እንደሚችል ስተውቀዋል።
በጦርነቱ የደረሱ ሰብዓዊ ቀውሶችና ድጋፎች
በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 7 ሺህ የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህ 3 ሺህ ህጻት መሆናቸውን በሃማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በእስራኤል በኩል የሃማስን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎየሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር 1 ሺህ 400 ላይ ቆሟል።
ቤተሰቦቻቸው በሃማስ የታገቱባቸው ሰዎች በቴል አቪቭ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፤ የሀገሪቱ መንግስት ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የተሻለ ስራዎችን እንዲሰራ ጠይቀዋል።
የተባበሩት መነግስታት ድርጅት፤ በጋዛ ያለው መጠለያ ጣቢያዎች መያዝ ከሚችሉት በላይ በሶስት እጥፍ ሰዎችን እያስተናገዱ መሆኑን እና ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል።
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍሊስጤም አምባሳደር የቦብም ድብደባው እንዲቆም እንዲያደርጉ ለዓለም ሀገራት መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍሊስጤም አምባሳደር በበኩላቸው በጋዛ ውስጥ እየተደረገ ያለው ጦርነት ከሀሃመስ እና ሀማስ ጋር ብቻ ነው ብለዋል።
የአውሮፓ ሀገራት መሩዎች በትናትናው አልት ሰዓታትን ከፈጀው ስብሰባ እና ክርክር በኋላ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ሰብዓዊ ድጋፎች መተላለፊያ እንዲከፈት ጥሪ ለማረብ ከስምምነት ደርሰዋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምዕራባውያን እስራኤል በጋዛ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ላይ ዝምታን በመምረጣቸው ተችተዋል፤ ዝምታን የመረጡበት ምክንያትም የፈሰሰው ደም የሙስሊሞች ደም በበመሆኑ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው እለት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቅ ውሳኔ ላይ ድምጽ ይሰጣል።