በ24 ሰዓታት ውስጥ 37 ሊባኖሳውያን ሲገደሉ፤ 151 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል
በእስራኤልና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል የነበረው ግጭት እየተካረረ መጥቶ አሁን ላይ ወደ ሙሉ ጦርነት ተሸጋግሯል።
የሄዝቦላህ እስራኤል ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ከአየር ድብደባው በተጨማሪ የፊትለፊት ውጊያም ተባብሶ ቀጥሏል።
ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል?
-እስራኤል ትናንት ብቻ በ24 ሰዓታት ውስጥ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ላይ ከ20 በለይ የአየር ድብደባዎችን መፈጸሟ ተነግሯል።
-በተለይም ትናንት ምሽት በቤሩት አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሄዝቦላህ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፤ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እንደነበሩም ታውቋል።
-የእስራኤል ጦር ምሽት በቤሩት በተጸመው የአየር ድብደባ የሄዝቦህል ተተኪ አመራር ይሆል የተባለውን የሄዝቦላ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ኃላፊ ሃሸም ሳፈዲንን ኢላማ ያደረገ እንደሆነ ተነግሯል።
-በቤሩት በተፈጸመው የአየር ድብደባ የጤና ተቋማት የቴልቪዥን ጣቢያ ኢላማ ነበሩ። በጤና ተቋም ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ቆሰለዋል።
-ባፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በመላው ሊባኖስ በአየር እና በምድር በተፈጸሙ ጥቃቶች 37 ሰዎች መሞታውን እና 151 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል
-በ24 ሰዓታት ውስጥ 28 የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቀዋል።
-ሄዝቦላህ በትናንትናው እለት ብቻ በእስራኤል ላይ ከ200 በላይ ሮኬቶችን የተኮሰ ሲሆን፤ በእስራኤል ጦር ይዞታዎች ላይደግሞ መድፍ እና ሮኬቶቸን መተኮሱ አስታውቋል።
የእስራኤል እና ሄዝቦላህ እግረኛ ጦር ውጊያ
ህዝቦላህ እስራኤል ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ከአየር ድብደባው በተጨማሪ የፊትለፊት ውጊያም ተባብሶ ቀጥሏል።
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባስ ውስጥ ከሚገኙ ተጨማሪ 20 አነስተኛ ከተሞች እና መንደሮች ዜጎች በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ሄዝቦላህ ትናነት ወደ እስራል ጦር ይዞታዎች 20 ምድፎችንና ሮኬቶችን መተኮሱን አስታውቋል፤ በትናንትናው እለት ብቻ 17 የእስራኤል ወታሮችን መግደሉን ገልጿል።
-የእስራኤል ጦር በትናነትናው እለት ተገድለዋል ስለተባሉ ወታደሮቹ እስካሁን ምንም ያላለ ሲሆን፤ ረቡዕ እለት የሞቱ ወታደሮቹ ቁጥር ግን 9 ደርሰዋል ብሏል።,
- ሄዝቦላህ ሁለት ተዋጊዎቹ በትናትናው እለት ከእስራኤል ጋር በነበረው ውጊያ እንደተገደሉበት አስታውቋል።