የእስራኤል ጦር በምስራቃዊ ሊባኖስ በፈጸመው ጥቃት ሶህሞር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል
እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችው የአየር ላይ ጥቃት ሁለተኛውን ከንቲባ ገደለች፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እንደቀጠለ ሲሆን በሊባኖስ መንግስታዊ ሀላፊነትን ያዙ ሃላፊዎችን ጨምሮ ንጹሃን እየተገደሉ ነው ተብሏል፡፡
በሂዝቦላህ ታጣቂዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት እያደረሰች መሆኗን የምትናገረው እስራኤል በምስራቃዊ ሊባኖስ በምትገኘው የሶህሞር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ አራት ዜጎችን እንደገደለች የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር ከሁለት ቀናት በፊት በተመሳሳይ በሊባኖሷ ናባቴህ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 16 ንጹሃን መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ሂዝቦላህ ወደ ሰሜናዊ እስራኤል በተኮሰው ሮኬት አንድ እስራኤላዊ መገደሉ ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ጦር እንደገለጸው ሂዝቦላህ የተኮሳቸው በርካታ ሮኬቶችን እንዳመከነ ገልጾ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መኖሪያ ቤት ኢላማ ያደረገ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መሰንዘሩንም አስታውቋል፡፡
በእስራኤል የተገደለው የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
በተመሳሳይ የእስራኤል ጦር አል መጋዚ በተሰኘው የስደተኞች ጣቢያ ለይ በሰነዘረው ጥቃት አንድ ነርስን ጨምሮ 11 ንጹሃን ተገድለዋል ተብሏል፡፡
የእስራኤል ጦር ከትናንት በስቲያ የሐማስ የፖለቲካ መሪን ያህያ ሲንዋርን በጋዛ መግደሉ አይዘነጋም፡፡
መሪው የተገደለበት ሐማስም ከፍልስጤም ውጪ ካሉ አባሎቹ ውስጥ አዲ መሪ ለመሰብሰብ እያሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡