እስራኤል በሰባት ወራት ዘመቻ ከሐማስ ታጣቂዎች መካከል 35 በመቶውን ብቻ መግደሏ ተገለጸ
ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ ታጣቂዎችን እየመለመለ መሆኑን የአሜሪካ ስለላ ተቋም አስታውቋል
65 በመቶው የሐማስ ታጣቂዎች አሁንም እንዳሉ ተገልጿል
እስራኤል በሰባት ወራት ዘመቻ ከሐማስ ታጣቂዎች መካከል 35 በመቶውን ብቻ መግደሏ ተገለጸ
ሀማስ ከሳባት ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
እስራኤል ሀማስ ላደረሰው ጥቃት እየሰጠችው ባለው ራስን መከላከል ዘመቻ ከ35 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊያን ተገድለዋል።
እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን ለመደምሰስ በሚል በተለያዩ ግንባሮች ዘመቻዋን እንደቀጠለች ሲሆን የአሜሪካ የስለላ ተቋም ቴልአቪቭ ከ30-35 በመቶ ያህል ታጣቂዎችን ብቻ ገድላለች ብሏል፡፡
የሐማስ ታጣቂዎች በተለያም በመሬት ውስጥ ዋሻ ያሉት ታጣቂዎች እስካሁን እንዳልተነኩ ፖለቲካ የአሜሪካ የስለላ ተቋማትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ታጣቂዎችን እንደመለመለ የተገለጸ ሲሆን አሜሪካ የእስራኤልን የጋዛ ዘመቻን ተችታለች፡፡
የአሜሪካ ጦር አዛዥ ጀነራል ቻርልስ ብራውን እስራኤል በጋዛ እየተከተለችው ያለው እቅድ ለውድቀት የሚዳርግ ነው ብለዋል፡፡
የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንዝ ስልጣን ሊለቁ እንደሚችሉ ተናገሩ
አዛዡ አክለውም እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን ለማጥፋት የጀመረችው ጥረት ላይሳካ እንደሚችል እና የተቆጣጠረቻቸውን ቦታዎች መልሳ ልታጣ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል፡፡
አሜሪካ ለእስራኤል በቀጥታ የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ መረጃዎችን ድጋፍ እያደረገች ሲሆን የአሁኑ ትችትም በፔንታጎን ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡
እንደ እስራኤል ባለስልጣናት መረጃ 128 ሰዎች አሁንም በሐማስ እጅ ታግተው የሚገኙ ሲሆን ታጋቾችን ለመልቀቅ እና የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ድርድሮች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ወይም አይሲሲ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት እንዲሁም የሐማስ ወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ተጠይቋል፡፡