እስራኤል በረመዳን ወቅት ወደ አል-አቅሳ በሚገቡ ሙስሊሞች ላይ የእድሜ ገደብ ጣለች
እስራኤል እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ የሆኑ ሙስሊሞችና ልጆቻቸው ከዌስትባንስ ወደ መስጂዱ እንዲገቡ እንደምትፈቅድ የኔታንያሁ ቢሮ ትናንት ሀሙስ ገልጿል

ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 ድንበር ጥሶ በደቡብ እስራኤል ጥቃት ከፈጸመ በኋላ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የፍልስጤማውያን የረመዳን ወር ክዋኔዎች ችግር ውስጥ ገብተዋል
እስራኤል በረመዳን ወቅት ወደ አል-አቅሳ በሚገቡ ሙስሊሞች ላይ የእድሜ ገደብ ጣለች።
እስራኤል በእስልምና እምነት ቅዱስ በሆነው የረመዳን ወር አርብ ቀናት ጥቂት እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ የሆኑ ሙስሊሞችና ልጆቻቸው በወረራ ከያዘችው ዌስትባንስ ወደ አል-አቅሳ መስጂድ ግቢ እንዲገቡ እንደምትፈቅድ የጠቅላይ ሚኒስቴር ኔታንያሁ ቢሮ ትናንት ሀሙስ ገልጿል።
ቢሮው ባወጣው መግለጫ ባለፈው አመት ተግባራዊ በሆነው አሰራር መሰረት ከዛሬ አርብ ጀምሮ "ውስን ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች" ይገባሉ ብሏል።
ወደ መስጂዱ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው ሰዎች ከ55 አመት በላይ የሆኑ ወንጆች፣ ከ50 አመት በላይ የሆኑ ሴቶችና እድሜያቸው እስከ 12 አመት የሆኑ ልጆች ናቸው። ወደ መስጂዱ ለመግባት ሁለም አማኞች ፍተሻ ይደረግባቸዋል ተብሏል።
"በእስራኤልዊ አረቦች ላይ ገደብ የለም" ሲል መግለጫ አክሏል።
መስጂዱ በአይሁዶች ሀርሃባይት ወይም ቴምፕል ተራራ እና በአለምአቀፍ ደረጃ ባሉ ሙስሊሞች ደግሞ አል-ሃራም አልሻሪፍ እየተባለ በሚጠራው የጥንታዊቷ የእየሩሳሌም ከተማ እምብርት ላይ ይገኛል።
ሙስሊሞች ቦታውን ከመካና መዲና ቀጥሎ ሶስተኛ ቅዱስ ቦታ አድርገው ይወስዱታል። አል-አቅሳ ሁለት የሙስሊም ቅዱስ ቦታዎች ማለትም የድንጋዩ ጉልላትና በ8ኛ ምዕተአመት የተሰራው አል-አቅሳ መስጂድን የያዘ ግቢ ስም ነው።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 ድንበር ጥሶ በደቡብ እስራኤል ጥቃት ከፈጸመ በኋላ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የፍልስጤማውያን የረመዳን ወር ክዋኔዎች ችግር ውስጥ ገብተዋል።