እስራኤል ከሐማስ ጋር ባደረገችው ጦርነት ከ67 ቢሊዮን ዶላር በላይ አውጥታለች ተባለ
ለ15 ወራት የዘለቀው የእስራኤል-ሐማስ ጦርነትን ማስቆም የሚችል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል
በጦርነቱ እስራኤል 850 ወታደሮቿን እንዳጣች ተገልጿል
እስራኤል ከሐማስ ጋር ባደረገችው ጦርነት ከ67 ቢሊዮን ዶላር በላይ አውጥታለች ተባለ፡፡
ሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት ከ15 ወራት በኋላ በግብጽ እና ኳታር አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በዚህ ጦርነት ከ45 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን እና ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊያን እንደተገደሉ በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ይህን ጦርነት የሚያስቆም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ጦርነቱ ያደረሳቸው ጉዳቶች እየተጠቀሱ ሲሆን እስራኤል 250 ቢሊዮን ሸክልስ ወይም ከ67 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወጪ አድርጋለች ተብሏል፡፡
የእስራኤል ብሔራዊ ባንክ በበኩሉ ሀገሪቱ በጦርነቱ ምክንያት አጥተዋለች የተባለው ገንዘብ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚል ገልጿል፡፡
በተለይም ጦርነቱ በእስራኤል ኢኮኖሚ እና ኢንዱስትሪዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ቢጠና ጉዳቱ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ባንኩ አስታውቋል፡፡
እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ተገለጸ
ዘ ታየም ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል በዚህ ጦርነት 850 ወታደሮቿ ተገድሎባታል፡፡
ከዚህ ውስጥ 329 ያህሉ ወታደሮች በእስራኤል-ጋዛ ድንበር ላይ የመጀመሪያው ጥቃት በተፈጸመበት ዕለት ብቻ የተገደሉ ናቸው ተብሏል፡፡
ቀሪዎቹ 405 ደግሞ የእስራኤል ወታደሮች የሐማስን ታጣቂዎች ለመደምሰስ በሚል ወደ ጋዛ ዘልቀው ከገቡ በኋላ የተፈጸመ ግድያ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ መንገዶች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተጨማሪ የእስራኤል ወታደሮች ሳይገደሉ እንዳልቀረም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡