የሄዝቦላ ታጣቂዎች ከደቡባዊ ሊባኖስ ካልወጡ የተኩስ አቁሙ እንደሚደፈርስ እስራኤል አስጠነቀቀች
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሄዝቦላ ከሊታኒ ወንዝ ባሻገር በ60 ቀናት ውስጥ እንዲሰፍር እና የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ለቆ እንዲወጣ ያዛል
ሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች የተስማሙበት የ60 ቀናቱ ቀነ ገድብ ሊጠናቀቅ 19 ቀናት ቀርተውታል
የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድን በደቡብ ሊባኖስ ከሚገኘው የሊታኒ ወንዝ ባሻገር ካልሰፈረ ከቡድኑ ጋር የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈርስ እንደሚችል እስራኤል አስጠነቀቀች፡፡
እስራኤል በሀማስ ላይ ጦርነት ባወጀችበት ማግስት ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ድጋፉን ለማሳየት ወደ ጦርነቱ የተቀላቀለው ሄዝቦላህ በቅርቡ ከቴልአቪቭ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መድረሱ ይታወሳል፡፡
በዚህ ስምምነት ሁለቱ ወገኖች ከህዳር 27 ጀምሮ ለ60 ቀናት ጦርነቱን ለማስቆም ተስማምተዋል።
በዚህ ጊዜ የሄዝቦላ ተዋጊዎች ከእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር 40 ኪሎ ሜትር እንዲያፈገፍጉ ሲጠበቅ የእስራኤል የምድር ጦር ከሊባኖስ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ለቆ እንዲወጣ ያዛል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሊጠናቀቅ 19 ቀናት የቀሩት ሲሆን ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከሊታኒ በስተደቡብ ያሉት የታጠቁ ቡድኖች የሊባኖስ ወታደሮች እና የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች ብቻ መሆን እንዳለባቸው ይደነግጋል።
እስራኤል እና ሄዝቦላህ የስምምነቱን ውል ጥሰዋል በሚል በተደጋጋሚ አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲወነጅሉ ቆይተዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ “በሰሜናዊ ድንበር የሚኖሩ እስራኤላውያንን ወደ መኖሪያቸው በሰላም ለመመለስ እና ዘላቂ ደህንነነታቸውን ለማረጋገጥ እስራኤል የተኩስ አቁሙን ሙሉ ለሙሉ ተግባራ ማድረጓን ትቀጥላለች” ብለዋል፡፡
ነገር ግን በኢራን የሚደገፈው ቡድን ከደቡባዊ ድንበር ካላፈገፈገ ስምምነት ብሎ ነገር የለም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በአካባቢው ከመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በስተቀር ታጣቂዎች እንዳይኖሩ እንዲሁም የሄዝቦላህ የጦር መሰረተ ልማቶች በሊባኖስ ጦር መፍረስ ቢጠበቅባቸውም ጦሩ እስካሁን ይህን አላደረገም ሲሉ ከሰዋል፡፡
የሂዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሰም በበኩላቸው የ60 ቀናት ጊዜን ማክበር እና ያለማክበር የቡድኑ ውሳኔ ነው ብለዋል።
“በእስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰት ዙሪያ ትዕግስታችን ሊያልቅ ይችላል ወይም ታግሰን ልንቀጥል እንችልም ይሆናል፤ ነገር ግን እርምጃ ለመውሰድ ስንፈልግ ቀድመው የሚያውቁት እነሱ ይሆናሉ” ብለዋል፡፡
ተኩስ አቁም ስምምነቱ ስራ ላይ ከዋለ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በግምት 100 ጊዜ መጣሷን በሊባኖስ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሪፖርት አመላክቷል፡፡
ሲኤንኤን ይዞት በወጣው ዘገባ ለጥቂት ጊዜያትም ቢሆን ጋብ ብሎ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ውጥረት ወደ ቀደመው ሁኔታ ለመመለስ እና ወደ በተረጋጋ ሁኔታ መጓዙን ለመወሰን የቀናት እድሜ ቀርተዋል ሲል አስነብቧል፡፡ሞስኮ በምስራቅ ዩክሬን ድል ሲቀናት፣ በምዕራብ ሩሲያ ደግሞ ውጊያው መጠንከሩ ተገለጸ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሩሲያ ኃይሎች ከፖክሮቭስክ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ 32 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የኩራክሆቭ ከተማ ተቆጣጥረዋል።
https://bit.ly/3W8YLBn