የእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር የጦር የመሳሪያ ድጋፍ ከቆመ “በጥፍራችንም ቢሆን እንዋጋለን” አሉ
አሜሪካ እስራኤል ራፋን ከወረረች "ወደ እስራኤል ቦምብ አንልክም" ማለቷ ይታወቃል
ኔታንያሁ የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ “እስራኤል ብቻዋን መቆም ትችላለች” ብለዋል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔታያሁ “አሜሪካ ጦር መሳሪያ ድጋፍ ካቋረጠች በጥፍራችንም ቢሆን እንዋጋለን አንጂ ወደኋላ አንመለስም” አሉ።
አሜሪካ የእስራኤል ጦር ወደ ራፋህ ገብቶ ጥቃት ከከፈተ ቀጣይ እርምጃዎችን እወስዳለሁ ስትል ማስጠንቀቋ ይታወቃል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ወደ ለእስራኤል ቦምብ እንደማትልክ እና እስራኤል ጦሯን በርካታ ስደተኞች ወደ ተጠለሉበት ራፋህ ከላከች ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰድ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ ራፋህ እንዳንገባ የሚከለክለን አካል የለም ያሉ ሲሆን፤ እስራኤል ውጊያውን እንደመትቀጥልበትም ተናግረዋል።
“ካስፈለገን ብቻችንን መቆም እንችላለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፤ “አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በጣቶቻችን ጥፍሮች እንዋጋለን” ብለዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንትም የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ያጣጣሉ ሲሆን፤ “ጠላቶቻችን ይሁን ወዳጆቻችን እስራኤል ለማንም የማትንበረከክት መሆኗን መረዳት አለባቸው” ብለዋል።
“ጠንካራ ሆነን በመቆመ ግባችንን እናሳካላን” ብለዋል የመከላከያ ሚኒስቱ ዮአቭ ጋላንት።
በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን የአሜሪካ ውሳኔ የሚያበሳጭ ነው ያሉ ሲሆን ዋሸንግተን ለእስራኤል የምትሰጠውን ድጋፍ ማቆም የለባትም ብለዋል።
ከአሜሪካ በተጨማሪም ካናዳ እና ሌሎችም የአውሮፓ ሀገራት ለእስራኤል የጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ እገዳ ጥለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሲኤንኤን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ " ለእስራኤል በሰጠነው ቦምብ ንጹሀን ተገድለዋል" ማታው ይታወሳል።
ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር ጦርነት የተቀሰቀሰው።
እስራኤል በሐማስ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ጥቃት ባለችው የመልሶ ማጥቃት ከ34 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል።