የአውሮፓ ህብረት እስራኤል ገዳይ ኃይልን እንደ "መጨረሻ አማራጭ" እንድትጠቀም ጠየቀ
ህብረቱ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግዛት ያለው ውጥረት ያሳስበኛል ብሏል
ባለፈው ሀሙስ በዌስት ባንክ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ ቢያንስ ዘጠኝ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ተብሏል
የአውሮፓ ህብረት እስራኤል ገዳይ ኃይልን እንደ "መጨረሻ አማራጭ" እንድትጠቀም ጠየቀ
የአውሮፓ ህብረት ቅዳሜ ዕለት በእስራኤል እና "በተያዙ" ግዛቶች ውስጥ እየጨመረ ያለውን ግጭት አስጠንቅቋል።
ህብረቱ እስራኤልን ገዳይ ኃይልን እንደ መጨረሻ አማራጭ ብቻ እንድትጠቀም አሳስቧል።
"የአውሮፓ ህብረት የእስራኤልን ህጋዊ የጸጥታ ስጋቶች ሙሉ በሙሉ እውቅና ይሰጣል" ብሏል።
ለዚህም የቅርብ ጊዜው የአሸባሪዎች ጥቃቶች ማስረጃ ይሆናል ያለው ህብረቱ በመግለጫው፤ ነገር ግን ህይወትን ለመጠበቅ ገዳይ ኃይል እንደ የመጨረሻ አማራጭ ብቻ መጠቀም አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል ሲል ተናግሯል።
የአውሮፓ ህብረት በእስራኤል እና "በተያዘው" የፍልስጤም ግዛት ያለው ከፍተኛ ውጥረት ያሳስበኛል ብሏል።
ሁለቱ ወገኖች ሁኔታውን እንዲያረግቡና እና በጸጥታ ጉዳይ መተባበርን እንደገና እንዲጀምሩ ጥሪውንም አቅርቧል። ይህም ተጨማሪ የግጭት ድርጊቶችን ለመከላከል አስፈላጊ ነው ሲል ህብረቱ በመግለጫው ጠቅሷል።
ባለፈው ሀሙስ በዌስት ባንክ ጄኒን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ ቢያንስ ዘጠኝ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከ20 በላይ ቆስለዋል ተብሏል።
ይህም ከአዲሱ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በዌስት ባንክ የተገደሉትን ፍልስጤማውያን ቁጥር 30 አድርሶታል።
ባለፈው ዓመት በዌስት ባንክ ከ150 በላይ ሰዎች በእስራኤል ወታደሮች ተገድለዋል ያለው ህብረቱ፤ ከነዚህም መካከል 30ዎቹ ህጻና ናቸው ብሏል።