የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በኋይት ሀውስ ሊገናኙ ነው
የመሪዎቹ ውይይት የሚካሄደው ለ15 ወራት የዘለቀውን የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ያስቆመው የስድስት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ነው
ትራምፕ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በአብዛኛው የተፈናቀሉትን ፍልስጤማውያንን ግብጽ እንድታስጠልላቸው እንደሚፈልጉ መናገራቸውንና ውዝግብ አስነስተዋል
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በኋይት ሀውስ ሊገናኙ ነው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር በኒያሚን ኔታንያሁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለ ሲመት ከፈጸሙ በኃይት ሀውስ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ይሆናሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁና ፕሬዝደንት ትራምፕ በየካቲት 4፣2025 በኋይት ሀውስ ተገናኝተው እንደሚመክሩ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የመሪዎቹ ውይይት የሚካሄደው ለ15 ወራት የዘለቀውን የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ያስቆመው የስድስት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ነው።
ትራምፕ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በአብዛኛው የተፈናቀሉትን ፍልስጤማውያንን ግብጽ እንድታስጠልላቸው እንደሚፈልጉ መናገራቸውንና ውዝግብ አስነስተዋል።
"እንዲወስዳቸው እፈልጋለሁ። በብዙ መልኩ እንረዳቸዋለን፣ እንደሚረዳን እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ ትራምፕ ስለግብጹ ፕሬዝዳንት አቡዱል ፈታህ አልሲሲ ተናግረዋል።
"ግጭትና አመጽ በሌበት ቦታ እንዲኖሩ እፈልጋለሁ" ሲሉ ትራምፕ በጋዛ ስለሚኖሩ ፍልስጤማውያን ተናግረዋል።
ትራምፕ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግብጽና ጆርጃን በጋዛ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን እንዲያስጠልሏቸው አስተያየት ሰጥተው ነበር።
ሁለቱ ሀገራትና ሌሎች የአረብ ሀገራት ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ሀሳብን ተቃውመዋል።
የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት በግብጽና ኳታር አደራዳሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድጋፍ ለበርካታ ወራት ከተካሄደ ድርድር በኋላ በተደረሰ የተኩስ አቁም ስምምነት ቆሟል።
ሀማስ በጥቅምት 23፣2023 በደቡባዊ እስራኤል ድንበር በመጣስ ጥቃት ፈጽሞ 1200 ሰዎችን ከገደለና 250 ሰዎችን ደግሞ አግቶ ከወሰደ በኋላ ነበር ጦርነቱ የተቀሰቀሰው።
እስራኤል በፈጸመችው መጠነሰፊ ጥቃት 47 ሺ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ለስድስት ሳምንታት በሚቆየው የመጀመሪያው ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት 33 የእስራኤል ታጋቾች በመቶዎች በሚቆጠሩ የፍልስጤማውያን እስረኞች ተለውጠው እንዲለቀቁ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ ተፈናቅለው የነበሩ ፍልስጤማውያን በእስራል የአየር ጥቃት ወደፈራረሰችው ጋዛ ከተማ እየተመለሱ ናቸው።