ሄዝቦላህ ጥቃቱን ማጠናከሩንና ትናንት ብቻ ከ20 በላይ የተሳኩ ዘመቻዎችን ፈጽሚያለሁ ብሏል
በእስራኤልና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በአየር ድብደባ እና በምድርጦር ተባብሶ እየተካሄደ ይገኛል።
እስራኤል በትናንትናው እለት በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ህጻናትን ጨምሮ 40 ሊባኖሳውያን መሞታቸውን የሊባኖስ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጦር አዳሩን ድብደባ ከፈጸባቸው አካባቢዎች መካከልም የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል አንዱ ነው ተብሏል።
በታይሬ ከተማ አርብ ምሽት በእስራኤል በተፈጸመ የአየር ድብደባም ቢያንስ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
በታይሬ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች ላይ የአየር ድብደባው ትናንት ቅዳሜ በቀጠሉ የእስራኤል የአየር ድብደባዎች ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸውን ነው የሊባኖስ ባለስልጣናት ያስታወቁት።
ትናንት ቅዳሜ በታሪካዊቷ ባልቤክ ከተማ ምስራቃዊ ክፍል በተደረገ የእስራኤል የአየር ድብደባዎች ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸውንም ነው የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር የገለጸው።
የእስራኤል ጦር በታይሬ እና በባልቤክ ከሞች የሚገኙ የሄዝቦላህ መሰረተ ልማቶች እና ወታደሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነው ያስታወቀው።
የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር የእስራኤል ጦር ባለፈው አንድ ዓመት በፈጸመው ጥቃቶች 3 ሺህ 136 ሰዎች መሞታውን እና 13 ሺህ 979 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጾ፤ ከሟቾች መካከል 619 ሶቶች እና 194 ህጻት እንደሆኑም አስታውቋል።
የሊባሱ ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶችን እየሰነዘረ መሆኑን አስታውቋል።
ሄዝቦላህ በትናትናው እለት ብቻ በእስራኤል ላይ 20 የተሳኩ ኦፕሬሽኖችን መፈጸሙን ያስታወቀ ሲሆን፤ ከአንድ ቀን በፊትም በደቡባዊ ቴል አቪቭ የሚገኝ የእስራኤል ወታራዊ ፋሪካ ላይ ጥቃት በፈጸሙን ገልጿል።