እስራኤል በበኩሏ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መስጠት ብሔራዊ አደጋ ያስከትልብኛል ስትል ስጋት ውስጥ ወድቃለች
እስራኤል ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ተስማማች።
አንድ ዓመት ያለፈው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶች ማስተናገዱን ቀጥሏል።
ባክሙት ለሩሲያ እና ዩክሬን ለምን አስፈላጊ ሆነች?
የአሜሪካ አጋሮች ዩክሬን በሩሲያ እየደረሰባት ያለውን ጥቃት ለመመከት የጦር መሳሪያ በገፍ እያስታጠቋት ሲሆን እስራኤል ገለልተኛ ሆና ቆይታ ነበር።
እስራኤል ገለልተኛ ሆና የቆየችው የጦር መሳሪያ ለዩክሬን ብትሰጥ በሶሪያ ያለው የሩሲያ ጦር፣ የእስራኤል የጦር ቴክኖሎጂ ምርቶች በኢራን እጅ ሊገቡ ይችላሉ እና ሌሎች ብሔራዊ የደህንነት ጉዳቶች ይደርሱብኛል የሚል ስጋት ገብቷት ቆይቷል ተብላል።
ይሁንና ጠቅላይ ቤንያሚን ኔትያንሁ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ እስራኤል ዩክሬንን ልትረዳ የምትችልባቸው መንገዶች ካሉ በሚል የፖሊሲ ጥናት ማድረጓ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት የጠቅላይ ሚንስትር ኔትያንሁ መንግሥት ሰው አልባ የጦር መሳሪያ ወይም ጸረ ድሮን ለዩክሬን እንዲሰጡ መፍቀዱ ተገልጿል።
ዩክሬን በበኩሏ እስራኤል ከድሮን ይልቅ አይረን ዶም የተሰኘውን የጸረ ባልስቲክ ሚሳኤል መሳሪያ እንዲሰጣት ጠይቃለች።
ዩክሬን ከሩሲያ የሚሰነዘሩባትን የድሮን ጥቃቶች 70 በመቶ መመከት መቻሏን ገልጻ በተለይም እስራኤል ሰራሽ የሆኑ ጸረ ሚሳኤል ድሮኖች እንዲሰጧት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርባለች።
እስራኤል በበኩሏ በዩክሬን ጥያቄ መሰረት አይረን ዶም የተሰኘውን ጸረ ሚሳኤል የጦር መሳሪያ መስጠት ከሩሲያ ጋር ሊያጋጨኝ እና ብሔራዊ ደህንነቴን አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ጥያቄውን ውድቅ ማድረጓ ተገልጿል።
እስራኤል ለዩክሬን እንዲሰጡ የፈቀደቻቸው የድሮን ጦር መሳሪያዎች በተለይም በዋና ዋና መሰረተ ልማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን መመከት ይችላሉ ተብሏል።
እስራኤል ውጊያ ላይ ባሉ የሩሲያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ማድረስ የሚያስችሉ የጦር መሳሪያዎችን ለዩክሬን መስጠት እንደማትችል አስታውቃለች