ሞሮኮ የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረችውን ምዕራባዊ ሰሀራን የግዛቷ አካል ያደረገችው በፈረንጆቹ 2975 ነበር
እስራኤል ምዕራባዊ ሰሀራ የሞሮኮ ሉአላዊ ግዛት ነች የሚል እውቅና ሰጥታለች።
እስራኤል ሞሮኮ በምዕራብ ሰሀራ ላይ ያላትን ሉአላዊነት እውቅና መስጠቷን አስታውቃለች። እስራኤል እውቅና በመስጠት ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ሀገር መሆን ችላለች።
የሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የሞሮኮ ንጉስ ሞሀመድ ስድስተኛ፣ ሞሮኮ በግዛቷ ላይ ያላትን ሉአላዊነት እውቅና የሚሰጥ ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ንታንያሁ መቀበላቸውን አስታውቋል።
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትር ንታንያሁ ጽ/ቤትም ዘግይቶ አረጋግጧል።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሊ ኮሀን "ምዕራባዊ ሰሀራን የሞሮኮ ግዛት አድርገን እውቅና መስጠታችን"የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ያጠናክራል ብለዋል።
እስራኤል እና ሞሮኮ ግንኙነት የጀመሩት በቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ አማካኝነት የአረብ እና እስራኤል ግንኙነትን ለማጠናከር በተደረሰው የአብረም ስምምነት ነበር።
ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው በፈረንጆቹ 2020 የፍልስጤም ተቃውሞ ሲነሳ ነበር።
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት የምታስተካክል ከሆነ የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ሞሮኮ በምዕራባዊ ሰሀራ ላላት የይገባኛል ጥያቄ እውቅና እንደምትሰጥም በፈረንጆቹ 2020 ቃል ገብቶ ነበር።
አሜሪካም በቃሏ መሰረት እውቅና ሰጥታለች።
ሞሮኮ የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረችውን እና ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ዘይት ይገኝባታል የተባለችውን ምዕራብ ሰሀራን የግዛቷ አካል ያደረገችው በፈረንጆቹ 2975 ነበር።
ነጻነት አቀንቃኝ የነበረው ፖልሳሪዎ ግንባር የሞሮኮን የመቀላቀል ተግባር በወቅቱ ተቃውሟል።