ሀማስ አቬራ መንግስቱን ጨምሮ ሁለት ታጋቾችን ሲለቅ፣ ተጨማሪ አራት ለመልቀቅ በሂደት ላይ ነው
ሀማስ እንደገለጸው ከሚለቀቁት ውስጥ በጋዛ በእስራኤል ጦር ተይዘው የታሰሩ 4ዐዐ ፍልስጤማውያንና በደርዘን የሚቆጠሩ ፍርደኞች ይገኙበታል

እስራኤል በምትኩ 602 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ከእስርቤቶቿ ትለቃለች ተብሎ ይጠበቃል
ሀማስ አቬራ መንግስቱን ጨምሮ ሁለት ታጋቾችን ሲለቅ፣ ተጨማሪ አራት ለመልቀቅ በሂደት ላይ ነው።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ሁለት ታጋቾችን መልቀቁንና ተጨማሪ አራት ታጋቾችን በመቶዎች በሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች በመለወጥ በዛሬው እለት ለመልቀቅ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ሮይተርስ ዘግቧል።
ሀማስ ታጋቾቹን የለቀቀው እስራኤል ከሰአታት በፊት ቀደም ብላ የተቀበለችው አስከሬን የሽሪ ቢባስ መሆኑን ካረጋገጠችና ውዝግቡ ከረገበ በኋላ ነው።
የ40 አመቱ ታል ሻሎም፣ የ39 አመቱ ቤተ-እስራኤላዊ አይሁድ አቬራ መንግስቱ በሀማስ ታጣቂዎች ወደ መድረክ ከወጡ በኋላ በደቡባዊ ጋዛ ራፋ ለቀይ መስቀል ተላልፈው የተሰጥተዋል። አራት ተጨማሪ ታጋች በማዕከላዊ ጋዛ በቅርቡ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዛሬ የተለቀቁትና የሚለቀቁት ስድስት ታጋቶች ሀማስ እና እስራኤል በደረሱትና ህዳር 19 ተግባራዊ መሆን በጀመረው የመጀመሪያ ዙር የተኩስ ኡቁም ስምምነት ከሚለቀቁት በህይወት ካሉት 33 ታጋቾች ውስጥ የመጨረሻዎቹ ናቸው።
አራቱ ታጋቾች ማለትም ሻሎም፣ የ27 አመቱ ኢሊያ ኮሄን፣ የ27 ኦመር ሼም፣ የ23 አመቱ ኦመር ወንከርት በሀማስ ታጣቂዎች የተያዙት ቡድኑ ጥቅምት 7፣2023 በደቡብ እስራኤል ድንበር ጥሶ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ነበር።
ሌሎቹ ሂሻም አልሰይድና አቬራ መንግስቱ ወደ ጋዛ ባልታወቀ ሁኔታ ከገቡ በኃላ ለአስርት አመታት ያህል በሀማስ ተይዘው ቆይተዋል።
በሀማስ እየተመራ ያለው ታጋቾችን የመልቀቅ ስነስርዓት ተመድን ጨምሮ በርካቶች "ታጋችን በማንገላታት" ትችት እያቀረቡበት ነው።
እስራኤል በምትኩ 602 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ከእስርቤቶቿ ትለቃለች ተብሎ ይጠበቃል። ሀማስ እንደገለጸው ከሚለቀቁት ውስጥ በጋዛ በእስራኤል ጦር ተይዘው የታሰሩ 4ዐዐ ፍልስጤማውያንና በደርዘን የሚቆጠሩ ፍርደኞች ይገኙበታል።
በሀማስ እና በእስራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በተሳሳተ አስከሬን ምክንያት የመናድ አደጋ ገጥሞት ነበር። ሀማስ ከልጆቿ ጋር ታግታ ተወሳዳ የሞተችው የቢባስ አስከሬን ነው ብሎ ለእስራኤል ማስረከቡና እስራኤል የእሷ አለመሆኑን ማረጋገጧ ውጦረት ፈጥሮ ነበር። ነገርግን ሀማስ ቤተሰቦቿ የቢባስ ነው ያሉትን አስከሬን ባለፈው አርብ እለት በማስረከቡ ውዝግቡ ተፈትቷል።
እስራኤልና ሀማስ፣ ሁሉም ታጋቾች በሚለቀቁበት፣ ዘላቂ ተኩስ አቁም በሚደረግበትና የእስራኤል ጦር ከጋዛ ጠቅልሎ በሚወጣበት ጉዳይ ሁለተኛ ዙር የተኩስ ከቁም ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።