ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ፡ ስልጣን ላይ እያሉ ፍርድቤት የቀረቡ የእስራኤል መሪ
ለአንድ አመት ያህል የቆየው የፍርድ ቤት ሂደት በፈረንጆቹ የሚመጣው ሃምሌ 19 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶበታል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድቤት ሲቀርቡ ስልጣን ላይ እያሉ ፍርድቤት የቀረቡ የመጀመሪው መሪ ሆነዋል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድቤት ሲቀርቡ ስልጣን ላይ እያሉ ፍርድቤት የቀረቡ የመጀመሪው መሪ ሆነዋል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀምና ከባለሀብቶች ሥጦታዎችን በመቀበል በሚሉ ክሶች ከተከሰሱ ቆይተዋል፡፡
ይሁንና ረጅም ጊዜ የወሰደው የፍርድ ሂደት አሁንም አልተቋጨም፡፡ ረጅም ዓመታትን እስራኤልን የመሩት ቢኒያሚን ኔታንያሁ (ቢቢ) በሀገራቸው ዜጎች እንደ ጀግና ሲወደሱ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሙሰኛ ይተቻሉ፡፡
አወዛጋቢዋ የእየሩሳሌም ከተማ የእስራኤል መዲና እንድትሆን የእስራኤል ተጽዕኖም ጎልቶ እንዲታይ አድርገዋል የሚሉ በአንድ ወገን፣ የለም ሙስና ይሰራሉ ቅንጡ የሚባሉ ስጦታዎችን ሳይቀር ከባለሀብቶች ይቀበላ የሚሉ ደግሞ በሌላ ጎን ቢቢ እየተባሉ የሚቆላመጡትን የሊኩይድ ፓርቲ መሪን ይተቻሉ፡፡
የማይካድ ሃቅ ግን አለ የሚሉት ተንታኞች አሜሪካ ኢምባሲዋን ከቴላቪቭ ወደ እየሩሳአሌም የቀየረችውም በቢቢ ዘመን አንደሆነም ይነሳል፡፡ ያም ሆነ ይህ የእስራኤል ዳኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያን ኔታንያን መጥሪያ ልከው ፍርድ ቤት አቁመዋል፡፡
በርካቶች በጎዳና ላይ ሲደግፏቸውም ሲነቅፏቸውም ታተዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸው “ቢቢ፣ የእስራኤል ንጉስ ፣ብቻዎትን አይጓዙም” ሲሏቸው ነቃፊዎቻቸው ደግሞ “የወንጀል ሚኒስትር ” እያሉ ተቃውመዋቸዋል፡፡ ትናንት ፍርድ ቤት ሄደው ቃላቸውን የሰጡት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በኃላፊነት ላይ ያሉ ፍርድ ቤት የቀረቡ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡
አሜሪካዊው የሕግ ባለሙያ አላን ደርሾዊትዝ በእየሩሳሌም ፖስት ላይ ባሰፈረው ጹሑፍ እስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሯን ፍርድ ቤት በማቆሟ ልታፍር ይገባል ሲል አስፍሯል፡፡ እርሱ እንዳለው ይህ ነገር የተደረገው ለተለየ የሚዲያ ሽፋን ሲባል እደሆነም ነው በጻፈው ጹሑፍ ላይ የገለጸው፡፡
በሀገራቸው ዳኞች ፊት ቀርበውም ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ እርሳቸውም ምንም በወንጀል የሚያስጠይቅ ስራ አልሰራሁም ነጻ ነኝ ሲሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ባጠለቋት ጭምብል ውስጥ ሆነው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለሚቀጥሉት 18 ወራት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የሚያገለግሉት “ቢቢ” ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከተቀናቃኛቸው ጋንዝ ጋር ስምምነት ካደረጉ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚቀጥሉ ቢያረጋግጡም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ግን አሁንም አልለቀቃቸውም፡፡
ለአንድ አመት ያህል የቆየው የፍርድ ቤት ውሎ በፈረንጆቹ ለፊታችን ሃምሌ 19 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ የእስራኤል የሕግ ተንታኞች ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ ወራትን አሊያም ዓመታትን ሊወስድ እንደሚችል ገምተዋል፡፡ ችሎቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከያ ጭምብል እንዲያወልቁና በቴሌቪዥን ሁኔታውን እንዲያብራሩ ጠይቀው ነበር፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የፍርድ ቤቱ ውሎ በጣም ጠበቅ ያለ እንደነበር ገልጸው “እዚህ ፍርድ ቤት የቆምኩት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኘ ነው” ማታቸውም ተዘግቧል፡፡ ኔታንያሁ ከ18 ወራት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ለተቀናቃኛቸው ጋንዝ ለማስረከብ የተስማሙ ሲሆን ሀገራቸው ከ10 ዓመታት በላይ መርተዋል፡፡