በሰዓት በሰዓት 370 ኪ.ሜ የሚጓዘው ድሮኑ ለ30 ሰዓታት አየር ላይ መቆየት ይችላል
“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮን የእስራኤል አየር ኃይል ከታጠቃቸው አደገኛ የአውደ ውጊያ መሳሪያዎች ውስጥ በቀዳሚነት ዪጠቀስ ነው።
በእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ የተመረተው ድሮኑ በተለያዩ ወታደራዊ ትልእኮዎች ላይ መሳተፍ ብቃቱን ማስመስከር እንደቻለ ይነገርለታል።
ሄሮን ቲፒ ድሮንን ከእስራኤል በተጨማሪ እንደ ጀርመን፣ አውስትራሊያ፣ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት እንደታጠቁጥ ይነገራል።
“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮንን ምን የተለየ ያደርገዋል…ʔ
ሄሮን ቲፒ ድሮን በየትኛውም አይነት የአየር ፀባይ ለ30 ሰዓታት ያክል መስራ ይችላ የተባለ ሲሆን፤ በሰዓት 370 ኪሎ ሜትር ፍጥነት መጓዝ እንደሚችልም ተነግሯል።
ድሮኑ ለተልዕኮ በሚሰማራበት ወቅት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከባህር ጠለል በላይእስከ 45 ሺህ ጫማ ድረስ ከፍ ብሎ በመብረር ከራዳር እይታ ውጪ ጥቃት መሰንዘር ይችላል።
ያለ ሰዎች ንክኪ በራሱ መነሳት እና ማረፍ የሚችው ድሮኑ፤ የሳተላይተ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀምም ከመቆጣጠሪያ ጣያው ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ መጓዝ ይችላ ተብሏል።