ድሮኑ እስከ 40 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ የሚገኝ ኢላማን በቀላሉ መምታት ይችላል
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያካሄደችው ባለው ጦርነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉ መሳሪያዎች ውስጥ “ዛላ ኬ.ዋይ.ቢ” ድሮን አንዱ እንደሆነ ይነገራል።
“ዛላ ኬ.ዋይ.ቢ” ድሮን የሩሲያው የጦር መሳሪየ አምራች ክላሽንኮቭ ግሩፕ ውስጥ የሚገኘው ዛላ ኤሮ ኩባንያ የሚመረት መሆኑን አርሚ ቴክኖሎጂ በድረ ገጹ አስነብቧል።
ድሮኑን የማምረት ንድፍ የተጠነሰሰው የሩሲያ ጦር በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2015 እስከ 2018 መካከል በሶሪያ ባደረጉት ውጊያ ላይ ተገኘ ልምድ መሆኑ ይነገርለታል።
ዶሮኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገውም በፈረንጆቹ በ2019 በዱባይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመከላከያ ኤግዚቢሽን ላይ እንደሆነም ይታወቃል።
ወታደራዊ ድሮኑ በተሞላለት ኢላማ መሰረት ጥቃት መሰንዘር እንደሚችል የተነገረ ሲሆን፤ በመሬት እና በውኃ ላይ ያሉ ኢላማዎችን ለመምታት ይችላል ተብሏል።
“ዛላ ኬ.ዋይ.ቢ” ድሮን ምን የተለየ ያደርገዋል?
የሶስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ድሮን ተልእኮውን በሚስጥር መፈፀም የሚችል ሲሆን፤ ለዚህም ይመስላል “ገዳዩ” አሊያም “አጥፈቶ ጠፊው” ድሮን የሚል መጠሪያ የተሰጠው።
የድሮኑ የክንፉ ርዝመት ከጫፍ እስከ ጫፍ 1 ነጥብ 21 ሜትር ስፋ ያለው ሲሆን፤ ሽንጡ ደግሞ 0.95 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 0.165 ሜትር መሆኑ ይነገራል።
አነስተኛ መጠን ያለው ድሮኑ የኤሌክትሪክ ሞተር የተገጠመለት ድሮኑ በሰዓት ከ80 እስከ 130 ኪሎ ሜትር መብበር እንደሚችልም ይነገራል።
የአንድ ጊዜ የአየር ላይ ቆይታው እስከ 30 ደቂቃ ነው የተባለለት ዶሮኑ፤ እስከ 40 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ በውኃ ላይም ይሁን በምድር ላይ የሚገኝ ኢላማን በቀላሉ መምታት ይችላል።
ድሮኑ በጥቃት ወቅት እስከ 3 ኪሎ ግራም ድረስ የሚመዝኑ ፈንጂዎች፣ ጥይቶች እና ሌሎች መሳሪያዎችን መሸከም የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
ድሮኑ ለወታደራዊ ተልዕኮዎች፣ ለስለላ እንዲሁም ለጥበቃ አገልግሎቶች መዋል የሚችል ሲሆን፤ ኢላማዎቹን በእይታ ብቻ መለየት እና በአይነት በአይነታቸው መመደብ የሚችልበት አርቲፊሻል እንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ነው።
ድሮኑ ጥቃት ከመፈፀም በዘለለም የአጥፍቶ ማጥፋት ጥቃትም ለመሰንዘር ይውላል የተባለ ሲሆን፤ በዚህም ድሮኑ ከሰማይ ላይ በቀጥታ ወደ ኢላማው ቁልቁል በመፈጥፈጥ ታንኮችን እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ያወድማል።