እስራኤል ከሐማስ እና ሂዝቦላህ ጋር ጦርነት መጀመሯን ተከትሎ አለኝ የምትላቸውን ባለ ስልጣናት ወደ ዚህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አስገብታለች
በእስራኤል የተሰራው የክፉ ቀን መሸሸጊያ
ከ11 ወራት በፊት ሐማስ ያልታሰበ ጥቃት በእስራኤል ላይ መጣሉን ተከትሎ ነበር በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነገሰው፡፡
ለትንሽ ቀናት ከቆየ በኋላ ወደ ስምምነት ይመጣሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ይህ ጦርነት መልኩን እየቀያየረ አንድ ዓመት ሊሆነው አንድ ወር ብቻ ቀሮታል፡፡
ይህን ተከትሎ እስራኤል ለክፉ ቀን መሸሸጊያ በሚል ከመሬት በታች የሰራችው መሸሸጊያ ባለስልጣናትን ከጥቃት መጠበቂያ አድርጋዋለች፡፡
የእስራኤል ወታደራዊ እና ሲቪል መሪዎች በሐማስ፣ ሂዝቦላህ ወይም ኢራን ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ወደ ክፉ ቀን መሸሸጊያው እንዲገቡ ማድረጓ ተገልጿል፡፡
ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ የተለያዩ ወሳኝ ስብሰባዎችን እና ወታደራዊ ትዕዛዝ ማስተላለፍ የሚያስችል መሰረተ ልማት የተገጠመለት ሲሆን ከየትኛውም ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች መከላከያዎች አሉትም ተብሏል፡፡
በእስራኤል በኤርትራውያን ስደተኞች መካከል በተከሰተ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉ
በመሀል እየሩሳሌም ተራራዎች ላይ መሰራቱ የተገለጸው ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ አገልግሎት እንደገባ ተገልጿል፡፡
ሻባክ የሚል ስያሜ ያለው ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ 95 በመቶ አካሉ በመሬት ውስጥ ሲገኝ ባንድ ጊዜ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከየትኛውም አደጋ ጠብቆ ያስጠልላል፡፡
እስራኤል ከሊባኖስ ጋር ጦርነት በገባችበት ከ18 ዓመት በፊት ይህንን የክፉ ቀን መሸሸጊያ እንደገነባችው እና መጠቀም እንደጀመረች ይታመናል፡፡
ሀገሪቱ የክፉ ቀን መሸሸጊያውን ለመስራት ቢሊዮን ዶላሮችን ወጪ እንዳደረገችበት ሲገለጽ የግንባታ ዲዛይኑ በአሜሪካ ዋሸንግተን ካለው ጋር ተመሳሳይነት እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡