“ካሪሽ የነዳጅ ስፍራ” በእስራኤልና ሊባኖስ መካከል የባለቤትነት ጥያቄ የሚነሳበት ቦታ ነው
የእስራኤል ጦር ፤ በሜድትራኒያን አከባቢ ነዳጅ ወደ ሚከማችበት ስፍራ ሲጓዙ የነበሩትን ሶስት የሂዝቦላህ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ሰው አለባ አወሮፕላኖቹ (ድሮኖቹ) የተነሱት ኪሊባኖስ ሲሆን፤ ሚሳዔል ታጥቀው የነበሩ ናቸው።
ሂዝቦላህ ባወጣው አጭር መግለጫም እንዲሁ ድሮኖቹ ወደ አካባው መላኩን አረጋግጧል ሲል ፍራንስ-24 ዘግቧል።
በዚህም በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላህ (የሺዓ ቡዱን) ፤ የአሁኑ በረራ አዲስ እንዳልሆነ ይልቁንስ አልፎ አልፎ ወደ አወዛጋቢው የካሪሽ ስፍራ የመስክ የስለላ ተልዕኮ በረራ እንደሚያደረግ ገልጿል።
"ተልዕኮው ተፈጽሟል" ያለው ሂዝቦላህ በመግለጫው ምንም እንኳ የእስራኤል ጣልቃ ገብነት ባይጠቅስም።
ባሳለፍነው ሳምንት፤ ሂዝቦላህ መሪ ሐሰን ናዝራህ እስራኤል በአከባቢው እንቅስቃሴ እንዳታደርግ የሃይል መከላከል እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ካሪሽ ተብሎ የሚታወቀውና ነዳጅ የሚገኝበት ስፍራ በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል የባለቤትነት ጥያቄ የሚነሳበት ቦታ ነው፡፡
እስራኤል ቦታው በተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት እውቅና የተሰጠው ልዩ የኢኮኖመኪ ዞን መሆኑ ስትገልጽ፤ ሊባኖስ በበኩሏ የተወሰነው ክፍል ይገባኛል ስትል ትሞግታለች፡፡
አሜሪካ በሀገራቱ መካከል ያለውን ቁርሾ ለማርገብ በልዩ መልእክተኛዋ አሞስ ሆችስቲን አማካኝነት የማሸማገል ጥረት እያረገች መሆኗም እንዲሁ የሚታወቅ ነው።