የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ሰርጥ እና በሊባስ የሀማስ ይዞታዎችን ደብድቧል
የእስራኤልዮር በሊባኖስ እና በጋዛ ሰርጥ ላይ ጥቃት ጥቃት መሰንዘሩ ተነግሯል።
ባሳለፍነው ረቡዕ በኢየሩሳሌም አል አቅሳ መስጊድ በእስራኤል ፖሊስ እና በፊሊስጤማውያን መካከል ግጭት መቀስቀሱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም በፍልስጤም የሚንቀሳቀሰው የሀማስ ታጣቂ ቡድን ከጋዛ ሰርጥ እና ከሊባኖስ ወደ እስራዔል የሮክት ጥቃቶችን እየሰነዘረ ይገኛል።
ይህንን ተከትሎም የእስራኤል ጦር 34 ሮኬቶች ወደተተኮሱበት ሰሜናዊ ሊባስ የሚገኝ ስፍራ ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።
የአየር ጥቃቱ በጋዛ የሚገኙ የሃማስ ታጣቂዎች ሪኬቶችን ማስወንጨፈጋቸውን ተከትሎ የተፈፀመ መሆኑንም የእስራዔል ጦር አስታውቋል።
ሃማስ እስካሁን ሮኬቶችን ውደ እስራኤል ስለመተኮሱ ያለው ነገር የለም።
ሆኖም ግን የሀማስ መሪ ኢስማዔል ሀኒየህ እስራዔል ጥቃት ስትሰነዝር ፍልስጤማውያን እጃቸውን አጣምረው ቁጭ ብለው አይመለቱም ሲሉ ተናግረዋል።
የእስራዔል ፖሊስ አል አቅሳ መስጊድ ወረራ መፈጸሙን ተከትሎ በስፍራው ያለው ውጥረግ በመቸመሩ ተነግሯል።