ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል የዓለማችን ዋነኛ ስጋት ነች አሉ
እስራኤል በሶሪያ እያደረሰች ያለውን ጥቃት እንድታቆም የጋራ እርምጃ ሊወሰድባት ይገባል ተብሏል
ሩሲያ እና ኢራን በእስራኤል ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል የዓለማችን ዋነኛ ስጋት ነች አሉ፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በድርድር ይፈታል ቢባልም አድማሱን እያሰፋ ቀጥሏል፡፡
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን እንዳሉት እስራኤል የመካከለኛው ምስራቅ እና የዓለማችን ሰላም ዋነኛ ጠላት ናት ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም እስራኤል በሶሪያ በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመች መሆኗን ተናግረው በቅንጅት ሊያስቆሟት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በሶሪያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ኢራን፣ ሶሪያ እና ሩሲያ የተቀናጀ ጥቃት በመክፈት ሊያስቆሟት ይገባልም ብለዋል፡፡
ሩሲያ እና ኢራን እስካሁን በፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ንግግር ዙሪያ ምላሽ አልሰጡም፡፡
የባህረ ሰላጤው ሀገራት እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት የአየር ክልላቸውን እንዳትጠቀም ከለከሉ
እስራኤል በተደጋጋሚ በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ጥቃቶችን ማድረሷ ይታወሳል፡፡
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል በጋዛ በሚኖሩ ፍልስጤማዊያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመች ነው በሚል በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እስራኤል ከሊባኖስ በኋላ ቱርክ የማጥቃት እቅድ እንዳላት መናገራቸውን ዶቸ ቪሌ ከሰሞኑ አስነብቧል፡፡
የሐማስ እና ሂዝቦላህ ዋነኛ ደጋፊ ናት የምትባለው ኢራን ከሰሞኑ እስራኤል በቴህራን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የአየር ክልላቸውን እንዳይፈቅዱ አስጠንቅቃለች፡፡