የሊባኖስ ጦር በእስራኤል እና ሄዝቦላ ጦርነት ለምን የዳር ተመልካች ሆነ?
እስራኤል በእግረኛ ጦር ሊባኖስን ከወረረች በኋላ የእስራኤል ኃይሎች እና የሄዝቦላ ታጣቂዎች በድንበር አካባቢ እየተዋጉ ሲሆን የሊባኖስ ጦር ግን ዳር ቆየ እያየ ይገኛል
ተወዳጁ የሊባኖስ ጦር በሀገሪቱ ባለው የሀይማኖት እና የፖለቲካ ልዩነት መሀል እንደድልድይ ሆነው ከሚያገለግሉ ጥቂት ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው
እስራኤል እና ሄዝቦላ ድንበር አካበቢ ሲዋጉ የሊባኖስ ጦር ዳር ቆሞ እየተመለከተ ነው።
እስራኤል በእግረኛ ጦር ሊባኖስን ከወረረች በኋላ የእስራኤል ኃይሎች እና የሄዝቦላ ታጣቂዎች በድንበር አካባቢ እየተዋጉ ሲሆን የሊባኖስ ጦር ግን ዳር ቆየ እያየ ይገኛል።
የሊባኖስ ብሔራዊ ጦር በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ በሚካሄድ ጦርነት የዳር ተመልካች ሲሆን ይህ የመጀመሪያ አለመሆኑን ኤፒ ዘግቧል። ተወዳጁ የሊባኖስ ጦር በሀገሪቱ ባለው የሀይማኖት እና የፖለቲካ ልዩነት መሀል እንደድልድይ ሆነው ከሚያገለግሉ ጥቂት ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው።
የጦር አባል የሆኑ በርካታ ኮማንደሮች ፕሬዝደንት እስከመሆን የደረሱባቸው በርካታ አጋጣሚዎችም አሉ።
ያረጁ ትጥቆች እና የአየር ኃይል መከላከያ ስርአት ያለው እና በአምስት አመት የኢኮኖሚ ቀውስ የመታው የሊባኖስ ብሔራዊ ጦር፣ እንደ እስራኤል ካሉ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁ ጦሮች ሊባኖስን ከእግረኛ ጦር እና ከአየር ጥቃት ለመከላከል ዝግጁነት የለውም።
ሄዝቦላ በሀገሪቱ ጦር ላይ ጥላ አጥልቶበታል።
የሊባኖስ ጦር አጠቃላይ ቁጥር 80ሺ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5ሺ የሚሆኑት በደቡብ ነው የተሰማሩት።
በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደሉት የቀድሞው የሄዝቦላ መሪ ሀሰን ነስረላህ እንደተናገሩት ከሆነ ሄዝቦላ 100ሺ ተዋጊዎች አሉት። በኢራን የተሰሩት መሳሪያዎቹም ብሔራዊ ጦሩ ከታጠቃቸው የዘመኑ ናቸው።
ሄዝቦላ ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን አጋርነት ለማሳየት ድንበር አሻግሮ ሮኬት ማስወንጨፍ ከጀመረበት ከጥቅምት 2023 ጀምሮ እስራኤል እና ሄዝቦላ ግጭት ውስጥ ገብተዋል። እስራኤል ባለፉት ሳምንታት በሊባኖስ ላይ ከባድ የአየር ድብደባ እና የእግረኛ ጦር ጥቃት ከፍታለች።
እስራኤል እንደገለጸችው ይህን ጥቃት የከፈተችው ሄዝቦላን ከድንበር አካባቢ ለማራቅ እና ጥቃት ሸሽተው የተፈናቀሉ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ወደ ቦታቸው ለመመለስ ነው። የእስራኤል ወታደሮች ድንበር ጥሰው ተኩስ ሲከፍቱ ሄዝቦላ በተኩስ ምላሽ ሲሰጥ ፣ የሊባኖስ ወታደሮች ከድንበር ኬላዎች ወደኋላ አምስት ኪሎሜትር አፈግፍገው ሰፍረዋል።
የእስራኤል ወታደሮች እስካሁን ብዙም አልገፉም። የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋጩት የእስራኤል ጦር የሊባኖስ ጦር በመሸገበት በቢንት ጂቢል ላይ በታንክ ተኩሶ አንድ ወታደር እና በዚሁ ቦታ በአየር ጥቃት ሁለት ወታደሮች በገደለበት ጥቅምት ሶስት ብቻ ነው።
የሊባኖስ ጦር በሁለቱም ጥቃቶች በተኩስ ምላሽ ሰጥቷል።
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የእስራኤል ጦር ወረራ አሁን ጦሩ ወደመሸገበት ቦታ የሚደርስ ከሆነ የሊባኖስ ጦር የተወሰነም ቢሆን ውጊያ ሊገጥም ይችላል።
የጦሩ "ተፈጥሯዊ እና ቀጥተኛ ተልእኮ ወደ ሊባኖስ ግዛት ሊገባ የሚችልን ጦር መከላከል ነው" ሲሉ ቀድሞ የሊባኖስ ጦር ጀነራል ሀሰን ጆኒ ተናግረዋል። "በእርግጥ የእስራኤል ጦር የሚገባ ከሆነ ይከላከላል፤ ነገርግን ባለው አቅም እና ራሱን በማይጎዳበት ሁኔታ ነው..."
የእስራኤል እና የሊባኖስ ጦር በአቅም ፈጽሞ የማይመጣጠን ነው።
እስራኤል በጎረቤቷ ሊባኖስ ላይ ወረራ ስትፈጽም በ50 አመታት ውስጥ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት በነበሩት በርካታ ወረራዎች ጦሩ የነበረው ሚና አነስተኛ ነበር። የሊባኖስ ጦር እና የሀገሪቱ ውስጣዊ ሁኔታ በ1975 በፈነዳው እና ለ15 አመታት በቆየው የእርስበርስ ጦርነት ምክንያት ተዳክሟል፤ በዚህ ምክንያት እስራኤል እና ሶሪያ የሀገሪቷን የተወሰነ ክፍል እስከመያዝ ደርሰው ነበር። ከእርስእበርስ ጦርነቱ በኋላ የእስራኤል ጥቃት ለመከላከል በሚል ትጥቅ ይዞ እንዲቆይ የተፈቀደለት ሄዝቦላ ብቻ ነበር።
ሄዝቦላ እና እስራኤል በ2006 የተዋጉ ሲሆን የሊባኖስ ጦር የእስራኤልን የአየር የበላይነት መቋቋም አልቻለም።