በቅርቡ ግንኙነት የጀመሩት ዩኤኢና እስራኤል በልማት ትብብር ላይ ተወያዩ
ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ መስከረም 15 የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት ተፈራርመዋል
እስራኤል ዩኤኢ መሰረቱን ግብጽ ባደረገው የኢነርጂ ጉባኤ እንድትካተት ሀሳብ አቅርባለች
እስራኤል ዩኤኢ መሰረቱን ግብጽ ባደረገው የኢነርጂ ጉባኤ እንድትካተት ሀሳብ አቅርባለች
በቅርቡ መደበኛ ግንኙነታቸውን የጀመሩት ሁለቱ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) የተፈጥሮ ጋዝን ወደ አውሮፓ መላክን ጨምሮ በመልካም ትብብርና የኢንቨስትመንት ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን እስራኤል በመግጫ አስታውቃለች፡፡
በፈረንጆቹ መስከረም 15 እስራኤልና ዩኤኢ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት ተፈራርመው ነበር፤ የእስራኤል የኢነርጂ ሚኒስትር ዩቫል ስቴኢንኒትዝ ስምምነቱ ለቀጣናው የኃይል ልማት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለው ነበር፡፡
መግለጫው ሚኒስትሩ ከዩኤኢ አቻቸው ጋር በኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታና በተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ የሚያጓጉዝበትን መስመር በመዘርጋት ለገበያ በማቅረብ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
እንደ መግለጫው ከሆነ ሚኒስትሩ ዩኤኢ መሰረቱን ግብጽ ባደረገው የኢነርጂ ጉባኤ እንድትካተት ሀሳብ አቅርበዋል፤ ይህም የተፈጥሮ ጋዝን ከምስራቅ ሜዲትራኒያን ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ ይረዳል ተብሏል፡፡
የእስራኤል የኢነርጂ ሚኒስትር እንዳሉት ዩኤኢጉዳዩን እመረምረዋለሁ ማለቷን ገልጸዋል፡፡
ግብጽ፣እስራኤል፣ ግሪክ፣ ቆብሮስ ፣ ጣሊያንና ጆርዳን ባለፈው ማክሰኞ የምስራቅ ሜዲትራኒያን የጋዝ ፎረም መስርተዋል፡፡