እስራኤል የመጀመሪያው ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት በ6 ሳምንታት እንዲራዘም መጠየቋ ተገለጸ
ሀማስ የማራዘሙን ጥያቄ መቃወሙንና መጀመሪያ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሁለተኛ ዙር ድርድር እንዲጀመር እንደሚፈልግ ተገልጿል

የመጀመሪያ ዙር ስምምነት በነገው እለት የሚጠናቀቅ ሲሆን እስራኤልም ሆነች ሀማስ ስምምነት ላይ ከልተደረሰ ምን ሊከሰት እንደሚችል ገልጽ አላደረጉም
እስራኤል የመጀመሪያው ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት በ6 ሳምንታት እንዲራዘም መጠየቋ ተገለጸ።
በግብጽ የሚገኘው የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ ስድስት ሳምንታት እንዲራዘም ጥያቄ ማቅረቡን ሮይተርስ የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ነገርግን ሁለተኛው ዙር ድርድር ጦርነቱን የሚያስቆሙ እርምጃዎች መውሰድን የሚያካትት ነው። የመጀመሪያ ዙር ስምምነት በነገው እለት የሚጠናቀቅ ሲሆን እስራኤልም ሆነች ሀማስ ስምምነት ላይ ከልተደረሰ ምን ሊከሰት እንደሚችል ገልጽ አላደረጉም።
ግብጽና ኳታር በአሜሪካ እየተደገፉ ለበርካታ ወራት ሞቅ ቀዝቀዝ ሲል ከቆየ ድርድር በኋላ እስራኤልና ሀማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርገዋቸዋል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ እስራኤል ወደ ሁለተኛው ዙር ድርድር እንድትገባ ጫና እንዲያደርጎባት አሳስቧል። እስራኤል የመጀመሪያው ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት ተራዝሞ ሀማስ በየሳምንቱ ሶስት እስረኞችን እንዲለቅና በምላሹ እስራኤል ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንድትለቅ እንደምትፈልግ ዘገባው የእስራኤል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የእስራኤል ጦር ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 የፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
የእስራኤል ጦር ሀማስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ያለውን አቅም ከታሰበው በላይ ይንቀው እንደነበረና "ንጹሃን እስራኤላውያን ከጥቃት የመከላከል ተልዕኮውን አለመወጣቱን" ትናንት የታተመው የእስራኤል ጦር ምርመራ ሪፖርት በማጠቃለያው ገልጿል።
ሀማስ ለአጠቃላይ ጦርነት ፍላጎት የለውም የሚለው ግምት ለረጅም ጊዜ በደንብ ሳይፈተሽ መቅሩቱ የእስራኤል ዝግጅትና ጥቃት የመከላከል አቅም ደካም እንዲሆን አድርጎታል ብሏል ሪፖርቱ።