![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/243-134908-img-20250209-122728-788_700x400.jpg)
ትራምፕ ወደ ኃይትሀውስ ከመግባታቸው በፊት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን በአጭር ጊዜ እንደሚያስቆሙት ቃል የገቡ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካላቸውም
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት ስለማቆሞ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር በሰልክ መነጋገራቸውን ሮይተርስ የኒው ዮርክ ፖስት ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ትራምፕ ባለፈው አርብ እለት ኤየርፎርስ ዋን ላይ ሆነው በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁለቱ መሪዎች ምን ያህል ጊዜ እንዳወሩ ተጠይቀው "ምንም አለማለት ይሻላል"ሲሉ መልሰዋል።
"እሱ(ፑቲን) የሰዎች ሞት እንዲቆም ይፈልጋል"ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ ስለጉዳሉ ከክሬሚሊንም ይሁን ከኃይትሀውስ መልስ አለማግኘቱን ገልጿል።
በጥር መጨረሻ አካባቢ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲን ከትራምፕ ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ መዘጋጀታቸውንና ሞስኮ ከዋሽንግተን የመጀመሪያ ቃል እየጠበቀች መሆኑን ተናግረው ነበር።
ባለው አርብ እለት ፕሬዝደንት ትራምፕ በቀጣይ ሳምንት የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ዘለንስኪን አግኝተው ጦርነቱን ስለማቆም ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ሩሲያ በየዩክሬን ላይ የጀመረችው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ሶሰት አመት ሊሞላው ሁለት ሳምንት ገደማ ይቀረዋል።
አብዛኞቹ የዩክሬናውያን የሆኑ ሰዎች በግጭቱ ተገድለዋል። ትራምፕ ለኒው ዮርክ ፖስት እንደተናገሩት "ከፑቲን ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ዝርዝር ጉዳዮችን አልተናገሩም።
"ፈጣን ነው ብየ አስባለሁ"ብለዋል ትራምፕ።
"በየቀኑ ሰዎች እየሞቱ ነው። የዩክሬኑ ጦርነት በጣም አስከፊ ነው። ጦርነቱ እንዲያቆሞ እፈልጋለሁ።"
ትራምፕ ወደ ኃይትሀውስ ከመግባታቸው በፊት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን በአጭር ጊዜ እንደሚያስቆሙት ቃል የገቡ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካላቸውም።