ልዩልዩ
በእስራኤል ፌስቲቫል ላይ ባጋጠመ መደርመስ ከ44 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ
አደጋው ያጋጠመው የፌስቲቫሉ ተመልካቾች የቆሙበት ደረጃ ተደርምሶ ነው ተብሏል
ፌስቲቫሉ በሰሜናዊ እስራኤል ሜሮን ተራራ ላይ የነበረ ሲሆን 10 ሺህ ሰዎች ተሳትፈውበታል
በእስራአል 100 ሺህ ሰዎች በተሳተፉበት ፌስቲቫል ላይ ባጋጠመ የደረጃ መደርመስ በትንሹ 44 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፌስቲቫሉ በሰሜናዊ አስራኤል ሜሮን ተራራ ላይ ዛሬ ሌሊት የተካሀደ ሲሆን ላግ ባኦማር የተሰኘውን የአይሁዶች በዓል ዋዜማ ላይ ነበር።
አደጋው ተመልካቾች የቆሙበት ደረጃ ተደርምሶ እንደደረሰ ቢነገርም የእስራኤል ቀይ መስቀል ግን አደጋው ያጋጠመው መድረኩ ላይ ከፍተኛ ተመልካች በመገኘቱ እንደሆነ ገልጿል።
በአደጋው የቆሰሉ ሰዎችን በአምቡላንስ እና በሂልኮፕተር ወደ አራት ሆስፒታሎች መወሰዳቸውም ተገልጿል።