ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ንግግር ሊያደርጉ ነው
ጆንሰን አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በኔታንያሁ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአብ ጋላንት ላይ ያቀረበውን የእስር ማዘዣ ጥያቄ አውግዘዋል
የሪፐብሊካኑ የአሜሪካ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግር እኔደሚያደርጉ ተናግረዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ንግግር ሊያደርጉ ነው።
የሪፐብሊካኑ የአሜሪካ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቅርቡ በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ንግግር እንደሚያደርጉ ባለፈው ሀሙስ እለት ተናግረዋል።
ኔታንያሁ በተወካዮች ምክር ቤት ንግግር እንደሚያደርጉ የተገጸው እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከፕሬዝደንት ባይደን ጋር አለመግባባት ውስት በገቡበት ወቅት ነው።
የጆ ባይደንን የእስራኤል ፖሊሲ የሚተቹት ጆንሰን በእስራኤል ኢምባሲ በተዘጋጀው የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ይህ "በችግር ጊዜ ለእስራኤል መንግስት ያለንን ጠንካራ ድጋፍ ያሳያል"ብለዋል።
በኔታንያሁ እና በባይደን መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ እስራኤል የአሜሪካን ጫና ወደ ጎን በመተው በግብጽ ድንበር የምትገኘውን ራፋን በማጥቃቷ ምክንያት ነው።
"የተወካዮች ምክርት ቤት ወይም ኮንግረሰ በሚያደርገው የጋራ ስብሰባ ኔታንያሁን እንደምናስተናግድ ሳሳውቃችሁ በደስታ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ጆንሰን።
ጆንሰን አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዚህ ሳምንት በኔታንያሁ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአብ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ያቀረበውን ጥያቄ አውግዘዋል።
አቃቤ ህጉ ባለፈው ጥቅምት ሰባት የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት እንዲፈጸም ባደረጉ የሀማሰ መሪዎችም ላይ የእስር ማዘዣ ጥያቄ አቅርቧል።
እስራኤል ከሀማስ መሪዎች ጋር መነጻጸሯም ክፉኛ አበሳጭቷታል።
እስራኤል፣ ሀማስ 253 ማገቱን እና 1200 ሰዎችን መግደሉን ተከትሎ በጋዛ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ከ35ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለስጣን ገልጸዋል።