የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር “የቤተሰቤን የምግብ ወጪዎች ራሴ ከኪሴ እሸፍናለሁ” አሉ
ውሳኔው ከስራቸው ለሚገኝ የጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት ማስታወቃቸውም ተናግሯል
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር ናፍታሊ መሮሪያ ቤታቸውን ዋና ጽ/ቤታቸው አድረገው ቢጠቀሙም ከትችት ያመለጡ አልቻሉም
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤነት ከአሁን በኋላ የቤተሰቦቻቸው የምግብ ወጪ ራሳቸው እንደሚሸፍኑ በትናንትናው እለት አስታውቀዋል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤነት ይህንን ያሉት ብዙ ገንዝብ አባክነዋል የሚል ትችት ከደረሰባቸው በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሰሞኑን ቻናል 13 የተባለ የእስራኤል ሚድያ ባሰራጨው ዘገባ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰራተኞቻቸው እንዲሁም ለቤተሰባቸው የሚያወጡት ገንዘብ የተጋነነና ፤ አባካኝ መሆናቸው የሚያሳይ ነው ማለቱ በበርካቶች ዘንዳ ቅሬታን ፈጥረዋል፡፡
መንበረ ስልጣን ከመጨበጣቸው በፊት ቢለየነር የነበሩት ናፍታሊ ቤነት ወጪው የተጋነነ ነው የሚለው ትችት ከህግ ውጭ የተደረገ ስላልሆነ ባይቀበሉትም የሰዎችን ሃሳብ ማክበር ስላለባቸው ከአሁን በኋላ የቤተሰቦቻቸው የምግብ ወጪ ራሳቸው እንደሚሸፍኑ በትናንትናው እለት አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ" ምንም እንኳን እኔና ቤተሰቦቼ ከህግ ውጭ ያደረግናው ስህተት ባይኖር ፤በተሰራጨው ወሬ ምክንያት በህዝብ የተፈጠረውን ቅሬታ እርዳዋለሁ፤ ስለዚህም ከአሁን በኋላ የቤተሰቦቼን ወጪ ራሴ ከኪሴ ለመሸፈን ወስኜያለሁ"ብሏል።
ውሳኔው ከስራቸው ለሚገኝ የጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት ማስታወቃቸውም ተናግሯል፡፡
"ወደዚህ ኃላፊነት የመጣሁት የተለየ ክብር ወይም ገንዘብ ፈልጌ አልነበርም ፤ እዚህች ወንበር ላይ ያለሁት የእስራኤልን ህዝብ ለማገልገል ብቻ ነው" ሲሉም ተናግሯል።
በጣም የተንደላቀቀ ኑሮ እንደሚኖሩ የሚነገርላቸው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ የለመዱትን ህይወት ለማስቀጠል እጅግ የተጋነነ በጀት እንደሚመድቡም ነው መረጃወች የሚጠቁሙት፡፡
ጠቅለይ ሚኒስትሩ ጥቅማ ጥቅምን ጨምሮ፤ የሀገሬው ሰዎች ከሚከፍሉት ግብር 26 ሺህ 400 ዶላር የሚሰጣቸው ሲሆን ከዚህም 7 ሺህ 400 ዶላር ለምግብና ቤተሰቦቻቸው የሚያውሉት ነው ተብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አባካኝ ናቸው የሚል ወቀሳ ከዚህም ከዚም ቢሰነዘርባቸውም ፤ ከሳቸው በፊት የነበሩት ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤንያሚን ናታንያሁ በጀት ከእሳቸው (ናፍታሊ) በሶስት እጥፍ የሚበጥ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ቤንያሚኒን ናታንያሁ በስልጣን ዘመናቸው፤ በጣም ውድ እቃዎች መግዛት፣ በውድ ሬስቶራንቶች መመገብ፣ ውድ በሚባሉ ቦታዎች ጸጉራቸው መስተካከል ያዘወትሩ እንደነበር የተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡ ነበር፡፡
ወርሃዊ የምግብ ወጪያቸውም ሳይቀር 11 ሺ 100 ዶላር እንደነበር ይገለጻል፡፡
ይሁን እንጂ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር ናፍታሊ፤ መንግስት ካዘጋጀለት ውጭ በቴልአቪቭ በሚገኘው መሮሪያ ቤታቸው ዋና ጽ/ቤታቸው አድረገው ቢጠቀሙም ከትችት ያመለጡ አይመስሉም፡፡
የጠቅላይ ሚኒስት ወርሃዊ ደሞዝ 16 ሺህ 500 ዶላር ሲሆን፤ ይህም የእስራኤል ዜጎች ከሚያገኙት ወርሃዊ ደሞዝ አንጻር እጅግ የተጋነነ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡
ቢልየነሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ፖለቲካው መድረክ መቀላቀላቸውን ተከትሎ ያስተዳድርዋቸው የነበሩ ሁለት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በ250 ሺህ ዶላር የሸጡ ብዙም የፋይናንስ ጥያቄ የሌላቸው መሪ መሆናቸው ይታወቃል፡፡