የአረብ ኢምሬትስ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት ጉባዔ በእስራኤል እየተካሄደ ነው
እስራኤል ከአራት የአረብ ጎረቤቶቿ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር እየመከረች ነው
ኢራን የዚህ ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ ስትሆን የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሌላኛው አጀንዳቸው ነው ተብሏል
አረብ ኢምሬትስን ጨምሮ 4 የዐረብ ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት ጉባዔ በእስራኤል በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን የተሳተፉ ሲሆን የኢራን የኒውክሌር ጉዳይን ጨምሮ የዩክሬን ጦርነት የጉባዔው አጀንዳዎች ናቸውም ተብሏል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ አዘጋጇ እስራኤልን ጨምሮ የአሜሪካ፣ የግብጽ፣ የአረብ ኢምሬትስ፣ የባህሬን እና የሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡በደቡባዊ እስራኤል ባለው ነጌቭ በረሃ በመካሄድ ላይ ያለው ይህ ጉባኤ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ፣ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እና ሌሎች አካባቢያዊ ጉዳዮች የውይይቱ አጀንዳዎች እንደሆኑ ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በእየሩሳሌም እያካሄዱ ያሌትን ሌላ ስብሰባ እንዳጠናቀቁ ወደ ነጌቭ በረሃ እንደሚጓዙ ይጠበቃል፡፡
የአረብ ኢምሬትስ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አበዱላህ ቢን ዛይድ በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት ከእስራኤል ጋር ባለው ወዳጅነት እና ልማት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ቆይታቸው በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና የወቅቱ የዓለም ትኩረት በሆነው የሩሲ እና ክሬን ጦርነት ጉዳይ መወያየታቸውን ዘገባው አክሏል፡፡
ኢራን በአካባቢው ተጽዕኖ የመፍጠር እንቅስቀሴ በማድረግ ላይ መሆኗ በዚሁ ጉባኤ ላይ የተገለጸ ሲሆን አካባቢውን የበለጠ ሰላማዊ ለማድረግም የመከላከያ ትብብሮችን ለማድረግ ማሰባቸውም ተገልጿል፡፡
በኢራን ኑክሌር ላይ እየተካሄደ ያለው ድርድር ኢራን የአካባቢው ሀገራትን ሰላም ሊጎዳ እንደሚችል እስራኤል ስጋት አላት፡፡
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢራን በፍጹም የኑክሌር አረር እንድትታጠቅ አንፈቅድም ሲሉ ተናረዋል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳድር ጊዜ እስራኤል ከጎረቤት እና ከአረብ ሀገራት ገር የአብርሃም ስምምነት የተሰኝ ግንኙነት መመስረቷ ይታወሳል፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረትም እስራኤል ከአረብ ኢምሬትስ፣ ከሞሮኮ እና ባህሬን ጋር አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን መጀመሯ ይታወሳል፡፡