በራፋህ በተፈጸመ ጥቃት ከተጎዱት ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በምትገኘው ራፋህ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
የእስራኤል ጦር በጥቃቱ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት፤ ጥቃቱ በራፋህ የሚገኝ የሃማስ ግቢን ኢላማ ያደረገ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ትክክለኛውን ኢላማ ጠብቆ የተፈጸመ ነው ብሏል።
በጥቃቱም የሃማስ የዌስት ባንክ ኃላፊን ጨምሮ በርካታ የብድኑ ኃላፊዎች እና አባላት መግደሉን ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።
ሆኖም ግን በጥቃቱ ንጹሃን ዜጎች እንደተጎዱ መረጃ እንዳለው ያስታወቀው የእስራኤል ጦር፤ ጉዳዩን እንደሚያጣራም አስታውቋል።
ጋዛን የሚያስተዳድረው የሃማስ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩሉ፤ እስራኤል በራፋህ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ35 በላይ ፍሊስጤማወያን መደገላቸውን አስታውቋል።
በተጨማሪም በርከታ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ያለው የጤና ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ፤ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ብሏል።
የእስራኤል የአየር ጥቃት የተፈጸመው በሺዎች የሚቆጠሩ ፍሊስጤማውያን በተጠለሉበት ቴል አል ሱልጣን መንደር አካባቢ ሲሆን፤ መንደሩ እስራኤልከሁለት ሳምንት በፊት ጥቃት በከፈተችበት በዱባዊ ራፋህ የሚገኝ ነው።
በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍሊስጤማውያን ጦርነቱን ሸሽተው ከግብጽ ጋር በምትወዋሰነው ጋዛ ተጠልለው እንደሚገኙም ነው የሚታወቀው።
የእስራኤል ሃማስ ጦርት ከስድስት ወራት በፊት ጥቅምት 7 የሃማስን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ሃማስ በወቅቱ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት 1 ሺህ 200 እስራኤላውያንን መግደሉ እና 250 ገደማ ሰዎችን አግቶ መውደሱ ይታወሳል።
እስራኤል የሃማስን ጥቃት ተከትሎ በጋዛ በከፈተችው ጥቃትም እስካሁን የተገደሉ ፍሊስጤማውያን ቁጥር ከ35 ሺህ የተሸገረ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ ሁለት ሶስተኛው ህጻናት እና ሴቶች ናቸው።