እስራኤል በሶሪያ ውስጥ በኢራን እና በኢራቅ የሚደገፉ ኢላማዎች ናቸው ያለቻቸውን ኢላማዎች ላይ ለአመታት ጥቃት ስታድርስ ቆይታለች
የእስራኤል ሚሳይሎች በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ አቅራቢያ በሚገኙት ኢላማዎች ያልተለመደ ጥቃት ማድረሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እስራኤል በሶሪያ ውስጥ በኢራን እና በኢራቅ የሚደገፉ ኢላማዎች ናቸው ያለቻቸውን ኢላማዎች ላይ ለአመታት ጥቃት ስታድርስ ቆይታለች፡፡ ኢራን የሶሪያውን ፕሬዝደንት በሸር አላሳድን የሚደግፍ ሃይል ከፈረንጆቹ 2011ጀምሮ ስተል መቆየቷ ይታወሳል፡፡
ሮይተርስ የሶሪያን ወታደራዊ ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው በደማስቆ ሱሪያ ብዛት ያላቸው ሚሳይሎች የየተኮሱ ሲሆን የሶሪያ አየር መከላከያ የተወሰኑትን ማክሸፍ ችሏል፡፤
"በጥቃቱ ወታደር ቆስሏል፤ አንዳንድ ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል" ሲል ምንጩን ጠቅሶ ዘገባው ገልጿል፡፡
የእስራኤል ጦር አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም ብሏል ሮይተርስ፡፡
የእስራኤል ጥቃቶች ብዙውን ጊዜ የሚከናወኑት በጨለማ ሽፋን ስር ነው።
ኢራን የአየር ማስተላለፊያ መስመሮችን በመጠቀም ሂዝቦላህን ጨምሮ በሶሪያ እና በሊባኖስ ውስጥ ላሉ አጋሮች የጦር መሳሪያ ለማድረስ የምታደርገውን ጥረት ለመግታት እስራኤል በሶሪያ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃቷን አጠናክራለች፡፡
ቴህራን በመሬት ዝውውሮች ላይ መስተጓጎል ተከትሎ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለጦር ኃይሏ እና አጋር ተዋጊዎች በሶሪያ ለማጓጓዝ በአየር ማስድረስን የበለጠ አስተማማኝ መንገድ አድርጋለች።