ቱርክ ለፍልስጤም ያላት ቅርበት ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ችግር ፈጥሯል
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ያኢር ላፒድ እና የቱርኩ ፕሬዝደን ታይፕ ኤርዶጋን በአሜሪካ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ተገናኝተዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ቢሮ እንደገለጸው የአሜሪካ አጋር የሆኑት ሀገራት መሪዎች በአካል ሲገኛኙ ከፈረንጆቹ 2008 ወዲህ ለመጀመሪ ጊዜ ነው ብሏል፡፡
የእስራኤል እና የቱርክ ግንኙነት በፍልስጤም ጉዳይ ሻክሮ የቆየ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ ኢነርጅ ቁልፍ የትብብር ዘርፍ ሆኖ ከወጣ በኋላ ግንኙነታቸው እየተሻሻለ መጥቷል፡፡
በቅርቡ ሁለቱም ሀገራት አዲስ አምባሳደር ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እስራኤል አራት ዜጎቿን - ሁለቱ ወታደሮች በፈረንቹ 2014 ጦርነት በኋላ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የጠፉትን ለመመለስ ፍላጎት እንዳሳየች የላፒድ ጽህፈት ቤት ተናግሯል።
የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክ ጋዛን የሚመራውን እና አብዛኛው ምዕራባውያን በአሸባሪነት የፈረጁትን የፍልስጤም እስላማዊ ንቅናቄ ሃማስ አባላትን አስተናግዳለች።
ቱርክ ለፍልስጤም ያላት ቅርበት ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ችግር ፈጥሯል፡፡ ቱርክ በፈረንጆቹ 2010 የእስራኤልን የባህር ሃይል በጋዛ ላይ የጣለውን እገዳ በጣለ ወቅት በተገደሉት 10 የቱርክ አክቲቪስቶች ተቆጥታለች፡፡